January 11, 2024 – Konjit Sitotaw 

በፍትህ ሚኒስቴር የሚሰጡ አገልግሎቶች በብሄራዊ መታወቂያ ብቻ እንዲሰጡ ሊደረግ ነው ተባለ።

በፍትህ ሚኒስቴር የሚሰጡ አገልግሎቶች በብሄራዊ መታወቂያ ብቻ እንዲሆኑ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የፍትሕ ሚኒስቴር አሳውቋል።

በዚህ መሰረት እያንዳንዱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በስሩ ያሉ ሰራተኞችና ተገልጋዮች አገልግሎቱ ሙሉ ለሙሉ ወደትግበራ ከመግባቱ በፊት ብሄራዊ መታወቂያ ለማግኘት እንዲመዘገቡ እና በእጃቸው እንዲያስገቡ አቅጣጫ መሰጠቱን መ/ቤቱ አመላክቷል፡፡

የብሄራዊ መታወቂያ ለማግኘት የት መመዝገብ ይቻላል?

ለብሄራዊ መታወቂያው በተመረጡ ባንኮች ፣በገቢዎች ሚኒስቴር፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ስር በሚገኘው የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት ፣በዋናው ፖስታ ቤት ፣አራት ኪሎ ቤተ-መንግስት መግቢያ ፓላስ ፓርኪንግ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ላይ አገልግሎቱ ማግኘት ይቻላል ተብሏል።

የፍትሕ ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች ፣ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አገልግሎት የሚያገኙ ጠበቆች እና ሌሌችም የሚመለከታቸው አካላት እንዲሁም አገልግሎት ፈልገው ወደተቋሙ የሚመጡ ግለሰቦች ለብሄራዊ መታወቂያ በመመዝገብ የካርድ ህትመትን በመያዝ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸው ተቋሙ አሳስቧል።