January 11, 2024

ኮሎኔሉ ብቻውን ቀረ!

የአራዊት ሰራዊቱ 73 ኛ ክ/ጦር በቡሬ ዳሞት ፋኖ ብርጌድ ክንደነበልባል አምበሳ ፋኖዎቻችን በተደጋጋሚ ተነርቷል። የቡሬ ዳሞት ብርጌድ ብዙ ነገሮችን በጭንቅላት ጨርሰው ወደ ውጊያ የሚያመሩ ለጠላት አደገኛ ፋኖዎች መሆናቸው ስጋት የፈጠረበት የክፍለጦሩ አዛዥ ኮሎኔል ድባቤ አበራ ቀደም ብሎ ከቡሬ ሸሽቶ ቲሊሊ ከትሟል።

ታዲያ ቡሬ ከተማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ካምፕ አድርጎ በፍርሃት ቆፈን ውስጥ የነበረው ሰራዊት በተሰራው ትንሽ ስራ እየተናደ ክፍለጦሩ የተለቀቀ ቤት መስሎ ኮሎኔሉ ብቻ ወደመቅረቱ መቃረቡን ባህርዳር ዊክሊክስ አረጋግጣለች።

ማክሰኞ ታህሳስ 30/2016 በርካታ የክፍለጦሩ አባላት ብሬና ስናይፕሮችን ይዘው ከካምፑ በመሰወር ፋኖን መቀላቀላቸውን የታወቀ ሲሆን ኮሎኔል ድባቤ በጠዋት ከእንቅልፉ ሲነቃ የሻምበል አዛዡ ሳይቀር ፋኖን መቀላቀሉን እንደመርዶ ተነግሮታል።

ኮሎኔሉ ይህን በፈገግታ ያለፈው ቢሆንም ረቡዕ ጥር 01/2016 ዓም ደግሞ ድጋሚ በርካታ የክፍለጦሩ አባላት የቡሬ ዳሞት አሳምነው ሻለቃን መቀላቀላቸው ተረጋገጠ። ከከዱት የሰራዊቱ አባላት ውስጥ 2 ኦሮሞ ወንድማማቾችና 8 የደቡብ ልጆች የሚገኙበት ሲሆን በአሳምነው ሻለቃ የፋኖ አባላት ደማቅ ወገናዊ አቀባበል እንደተደረገላቸው ታውቋል። እንግዲህ ኮሎኔል ድባቤ ይህችን ቁርስ ከጨጨብሳ ጋር ቀላቅለህ በባዶው ሳሎንህ ውስጥ አጣጥማት።

መልካም ቁርስ ኮሎኔል!
(ፎቶ፦ የቡሬ ኢንዱስትሪ ፓርክ)
©BW