የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚይ ሽኩሪ ዛሬ ኤርትራ አስመራ ገብተዋል።
ሚኒስትሩ አስመራ ሲደርሱ የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ ተቀብለዋቸዋል።
በኃላም ሚኒስትሮቹ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።
ውይይቱ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ሲሀን የሁለቱን ሀገራት ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በሚቻልበት ሁኔታ እና በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ በተለይም በአፍሪካ ቀንድ ጉዳይ ላይ ምክክር አድርገዋል ተብሏል።
ከዚህ በተጨማሪ ፤ የሱዳን ጉዳይ ፣ የቀይ ባህር ደህንነት እና በጋዛ ሰርጥ ስላለው ጦርነት ውይይት ማድረጋቸው ተሰምቷል።
ከቀናት በፊት የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ወደ ኤርትራ በማቅናት ከፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ምክክር ማድረጋቸው ይታወሳል።
