
ከ 2 ሰአት በፊት
ፕሪሚየር ሊጉ ተመልሷል።
በዚህ ሳምንት ኒውካስልን ከማንቸስተር ሲቲ፤ዩናይትድን ደግሞ ከቶተንሃም አገናኝቷል።
የቢቢሲው እግር ኳስ ተንታን ክሪስ ሱተን የጨዋታዎቹን ግምት እንደሚከተለው አስቀምጧል።
አርብ
በርንሊ ከ ሉተን
ይህን ጨዋታ መገመት ቀላል አይሆንም።
በርንሊ በውድድሩ መጀመሪያ አካባቢ በኪኒልዎርዝ ሮድ ሉተንን ማሸነፍ ችለው ነበር። ይህን ጨዋታ በሜዳቸው ማሸነፍ ይችላሉ ብዬ ግምት እንዳልሰጠ በሜዳቸው ያላቸው አቋም በጣም የወረደ ነው።
እስካሁን በሜዳቸው 30 ነጥብ ማግኘት ሲኖርባቸው ማሳካት የቻሉት 3 ብቻ ነው።
ይህ ጨዋታ ለቪንሰንት ኮምፓኒ እጅግ ወሳኝ ነው።
በሌላ በኩል ሉተን ከቅርብ ግዜ ወዲህ የሚቀመሱ አልሆኑም። በቅርብ ሳምንታት ኒውካስልን እና ሼፊልድ ዩናይትድን ማሸነፋቸው ይታወሳል።
ጨዋታው ሉተን ባያሸንፍም ይሸነፋል ብዬ ግን አልገምትም።
ግምት፡ በርንሊ 1 1 ሉተን
ቅዳሜ

ቼልሲ ከ ፉልሃም
ቼልሲዎች በተከታታይ ሦስት ጨዋታዎችን ማሽነፍ ቢችሉም በሳምንቱ አጋማሽ በካራባኦ ዋንጫ በሚድልስብራ ተሸንፈዋል።
ቡድኑ በርካታ ተጫዋቾችን ቢገዛም ከባለፈው ዓመት አንጻር ብዙ መሻሻል አላሳየም።
ፉልሃምም በመጨረሻው የሊጉ ጨዋታው አርሰናልን ያሸንፍ እንጂ ከሜዳው ውጭ አመርቂ አይደለም።
በዚህ ጨዋታ ቼልሲ ሦስቱን ነጥብ የሚያሳካ ይመስለኛል።
ግምት፡ 2 – 1
ኒውካስል ከ ማንቸስተር ሲቲ
ኒውካስል በዚህ ሰዓት ማንቸስተር ሲቲን መግጠሙ ዕድለ ቢስ ያደርገዋል።
ሲቲ ከኬቪን ደ ብራይን መመለስ በኋላ አዲስ መልክ ይዞ ስለመቅረቡ የምንመለከትበት ጨዋታ ነው።
ኒውካስል በሊጉ ሦስት ተከታታይ ጨዋታዎችን ተሸንፈዋል።
ካላቸው አጨዋወት አንጻር ኒውካስሎች አነስተኛ ጎል ሲያስቆጥሩ ሲቲ ደግሞ ብዙ ያስቆጥራል።
ግምት፡ 1 – 3
እሑድ

ኤቨርተኖች ያለፉትን ሦስት የሊግ ጨዋታዎች ተሸንፈዋል። አስቶን ቪላ በአንዳንድ ጨዋታዎች አሳማኝ አይደለም።
ከወራጅ ቀጠና በአንድ ነጥብ ብቻ ከፍ ብሎ የሚገኘው አቨርተን ከዚህ ጨዋታ ነጥብ ማግኘት አጥብቆ ይፈልጋል።
በዚህ ጨዋታ ኤቨርትን ነጥብ እንዲያገኝ ፍላጎት አለኝ።
ግምት፡ 1 – 1

ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ቶተንሃም
ብዙ የፕሪሚየር ሊግ በድኖች ዘንድሮ ወጥ መሆን አቅቷቸዋል። ማንቸስተር ዩናይትድ ደግሞ የዚህ ዋነኛ ማሳያ ነው።
ቀያይ ሴጣኞቹ ቪላን እንደምንም አሸንፈው በፎረስት መሸነፋቸው ይታወሳል።
ቶተንሃም ጎሎችን የማስቆጠር ችግር ባይኖርበትም የአምበሉ ሰን ሁይንግ-ሚን ወደ እስያ ዋንጫ መሄዱ ስጋት ፈጥሮብኛል።
ቶተንሃም ዘንድሮ በተመሳሳይ አጨዋወት ወደ ሜዳ የሚገባ ሲሆን ይህንን ጨዋታ እንደሚያሸንፍ እገምታለሁ።
የቶተንሃም አጨዋወት ለማንቸስተር ዩናይትድ ፈታኝ እንደሚሆን እገምታለሁ።
ግምት፡ 1 – 3