
ከ 5 ሰአት በፊት
ቡሩንዲ ለአማፂያን የገንዘብ ድጋፍ ታደርጋለች በሚል ከሩዋንዳ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር ዘግታለች ።
ባለፈው ታህሳስ ሬድ ታባራ የተባለው የብሩንዲ አማፂ ቡድን በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ድንበር አካባቢ 20 ሰዎችን ገደለዋል።
የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ክሱን ውድቅ ቢያደርጉም የብሩንዲ መንግሥት ግን “መጥፎ ጎረቤት” ሲል ፈርጇቸዋል።
የቡሩንዲ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ማርቲን ኒቴሬሴ “እስኪያለውጥ ድረስ [ካጋሜ] ከእሱ ጋር ያለንን ግንኙነት አቁመናል” ብለዋል።
የቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ ጥቃቱን ተከትሎ በታህሳስ ወር ሩዋንዳን ከሰዋል።
ቡሩንዲ የድንበር በሯን በመዝጋቷ አዝኛለሁ ሲል የሩዋንዳ መንግሥት ምላሽ ሰጥቷል።
የድንበር መዘጋቱ የቀጣናዊ ትብብር መርሆዎችን እና የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብን ውህደት መርህን የሚጥስ “ውሳኔ” ነው ብሏል።
- በኢትዮጵያ በድርቅ የተጎዱ ‘4 ሚሊዮን ዜጎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል’11 ጥር 2024
- ተመራማሪዎች ከሰው ዐይነ ምድር የአውሮፕላን ነዳጅ ፈጠሩከ 6 ሰአት በፊት
- ሶማሊያዊያን የኢትዮጵያ እና የሶማሊላንድ ስምምነትን በመቃወም አደባባይ ወጡ11 ጥር 2024
ሬድ ታባራ በታህሣሥ የተፈፀመውን ጥቃት መፈጸሙን ቢያምንም የተገደሉት ዘጠኝ ወታደሮችን እና አንድ የፖሊስ መኮንን ብቻ ናቸው ብሏል።
ቡድኑ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ደቡባዊ አቅጣጫ ከብሩንዲ ጋር በሚያዋስነው የኪቩ ግዛት ይንቀሳቀሳል።
የድንበር መዘጋቱ የመሬት እና የአየርን ድንበርን ያካተተ ስለመሆኑ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም።
ብሩንዲ እአአ በ2015 በፖለቲካ ውጥረት እና በኋላም በኮቪድ-19 ምክንያት ከሩዋንዳ ጋር የሚያዋስናትን ድንበሯን ዘግታለች። ከሰባት ዓመታት በኋላ ድንበሮቹ እንደገና ተከፍተዋል።
በዚያን ጊዜ በምድር መሻገር ብቻ ተፈቅዶለታል። ነገር ግን የአገሪቱ አየር መንገድ ርዋንድ ኤየር ወደ ቡሩንዲ የሚያደርገውን የንግድ በረራ አላቆመም።
ሩዋንዳ እና ቡሩንዲ ተመሳሳይ ቋንቋ፣ የዘር ስብጥር እና የቅኝ ግዛት ታሪክ ቢኖራቸውም ግንኙነታቸው የሻከረ ሆኖ ዘልቋል።
