
12 ጥር 2024, 16:49 EAT
የአፍሪካ ካቶሊክ ጳጳሳት የሮማው ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎችን በተመለከተ ያወጡትን አዋጅ ተቃወሙ።
ጳጳሳቱ እንደሚሉት ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ ቄሶች የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያንን መባረክ ይችላሉ ሲሉ ያወጡት አዋጅ “ከፈጣሪ ፈቃድ የወጣ ነው።”
በአፍሪካ ያሉ የካቶሊክ ጳጳሳት ሕብረት የሆነው በምሕፃረ ቃሉ ሴካም የተሰኘው ማሕበር ባወጣው መግለጫ ነው ይህን ያለው።
መግለጫው፤ ቫቲካን የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያንን ይሁንታ መስጠቷ “ተገቢ አይደለም” ይላል።
“ቤተክርስቲያኗ እንደምታስተምረው የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን ድርጊት «ከተፈጥሮ የሚጣረስ ነው» ነው ከተፈጥሮ ሕግም የወጣ ነው” ይላል መግለጫው።
የሴካም ፕሬዝደንት ካርዲናል ፍሪዶሊን አምቦንጎ እንደሚሉት መልዕክቱ በሊቀ ጳጳሱ የፀደቀ ስለሆነ ተግራባራቸውን በካቶሊክ ቤተክርስትያን መሠረት ማካሄድ ይቀጥላሉ።
የሮማ ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ የቤተ-ክርስትያኗ ካህናት ለተመሳሳይ ፆታ ጥንዶች ቡራኬ መስጠት እንዲችሉ የፈቀዱት ባለፈው ወር ነው።
ይህን ተከትሎ የካቶሊክ ቤተክርስትያናት የተዘበራረቀ ስሜት አንፀባርቀዋል።
የተመሳሳይ ፆታን እንደ ወንጀል ከሚቆጥሩ 64 የዓለማችን ሀገራት መካከል ግማሹ በአህጉረ አፍሪካ ነው የሚገኙት።
- ፖፕ ፍራንሲስ የሮማ ካቶሊክ ቄሶች ለተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎች ቡራኬ መስጠት ይችላሉ አሉ19 ታህሳስ 2023
- አፍሪካዊቷ ደሴት ኬፕ ቨርድ ከወባ በሽታ ነፃ ወጣች12 ጥር 2024
- ኢጋድ በኢትዮጵያና ሶማሊያ ውዝግብ ጉዳይ ለመነጋገር አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ12 ጥር 2024
የሊቀ ጳጳሰሱ ዜናው በተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን ዘንድ ትልቅ እመርታ ተደርጎ ተወስዷል።
የሮማን ካቶሊክ ቤተ-ክርስትያን መሪ እንዳሉት የቤተ-ክርስትያኒቱ ቄሶች የተመሳሳይ ፆታ “ያልተለመዱ” ጥንዶችን በአንዳንድ ሁኔታዎች ቡራኬ መስጠት እንዲችሉ ፈቅዳለች።
ነገር ግን ቫቲካን እንዳለው ይህ የሚሆነው በተለምዶ በቤተክርስትያኗ በሚካሄዱ ሥነ-ሥርዓቶች ላይ አይደለም።
ቫቲካን አክሎ አሁንም ቢሆን ትዳር በአንድ ወንድና ሴት መካከል የሚደረግ ሥነ-ሥርዓት እንደሆነ ነው የምናየው ብሏል።
ቫቲካን፤ ይህ መልዕክት “ከፈጣሪ የተላከና እሱ ሁሉንም እንደሚቀበል የሚያሳይ ነው” ብሎ በመመሪያው መሠረት ቄሶች ሁኔታውን በዝግታ እያጤኑ እንደሚተገብሩት ጠቁሟል።
መመሪያውን ያስተዋወቁት ካርዲናል ቪክተር ማኑዌል ፈርናንዴዝ አዲሱ ትዕዛዝ “በቀደመው ባሕላዊ የቤተ-ክርስትያኒቱ የትዳር መመሪያ ላይ አሁንም ጥብቅ ነው” ብለዋል።
ካርዲናሉ አክለው ሊቀ ጳጳሱ ካለሳቸው የቤተ-ክርስትያኗን ተቀባይነትን “የማስፋት” ዓላማ ጋር በተያያዘ ቄሶች አሁን ለወትሮው ኃጥያት ተብለው የሚቆጠሩ ግንኙነቶችን መባረክ ይችላሉ ብለዋል።
አዲሱ መመሪያ እንደሚለው “ቡራኬ የሚቀበሉ ሰዎች ከዚህ ቀደም ፍፁም የሆነ ሞራል እንዲኖራቸው አይጠበቅም።”
በካቶሊክ ቤተ-ክርስትያን መሠረት ቡራኬ ማለት ፀሎት አሊያም ተማፅኖ ሲሆን ቄሶች ፈጣሪ አንድን ግለሰብ አሊያም ሕዝብን እንዲያስብ የሚማፀኑበት ሥነ-ሥርዓት ነው።
አዲሱ መመሪያ ምንም እንኳ ቫቲካን ከዚህ ቀደም ካለው አተያይ ሲነፃፀር ላላ ያለ ቢሆንም አሁንም የቤተ-ክርስትያኗ አቋም እንዳልተቀየረ የሚያሳይ ነው።
በአውሮፓውያኑ 2021 “ፈጣሪ ኃጥያትን ስለማይባርክ” ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያንን ቄሶች አይባርኩም ብለው ነበር።
ነገር ግን ባለፈው ጥቅምት ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያንን መባረክ በተመለከተ ሐሳባቸውን ሊቀይሩ እንደሚችሉ ጠቁመው ነበር።
በተለያዩ ሃገራት የሚገኙ ሊቃነ-ጳጳሳት ከዚህ ቀደም የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያንን ቄሶች እንዲባርኩ ፈቃድ ሰጥተው ነበር።