በኔዘርላንድስ ሄግ የሚገኘው ዓለም አቀፉ ሸንጎ

13 ጥር 2024, 08:34 EAT

በዓለም አቀፉ የፍትሕ ፍርድ ቤት የደቡብ አፍሪካ እና እስራኤል ክርክር ተሰምቷል።

እስራኤል በጋዛ እየፈጸመች ያለው ጥቃት “የአንድን አገር፣ ዘር፣ ሃይማኖት አባላት በአጠቃላይ ወይም በከፊል ለማጥፋት የተቃጣ ነው” የሚለውን ዳኞች የሚወስኑ ይሆናል።

ይህ የሚወሰነው በእአአ 1948 በተደረሰው ስምምነት ነው።

ሀለቱም ወገኖች ስሜታዊ ንግግር በፍርድ ቤት አሰምተዋል።

1,300 እስራኤላውያን ሲገደሉ 240 በሐማስ ታግተው ተወስደዋል።

በእስራኤል ጥቃት በአብዛኛዎቹ ሴቶችና ሕጻናት የሆኑ 23,350 ሰዎች እስካሁን ተገድለዋል።

ደቡብ አፍሪካ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤቱ የወሰደችው እስራኤል ፍልስጤማውያን ንጹኃንን በመግደሏና የጋዛን መሠረተ ልማት በማውደሟ ነው።

ከጠበቆቹ አንዱ አዲላ ሐሲን “ግድያው የፍልስጤማውያንን ሕይወት የማውደም ነው” ብለዋል።

በጋዛ ጦርነቱ እንዲቀጥል መተው የለበትም ሲሉ ተከራክረዋል።

“አጠቃላይ የቤተሰብ ትውልዶች ይጠፋሉ” ያሉት አየርላንዳዊው ጠበቃ ብሊን ኒ ጋሊግህ ናቸው።

ብዙ የጋዛ ሕጻናት “አካላዊ ጉዳት ይደርስባቸዋል፣ ቤተሰብ አልባም ይሆናሉ” ሲሉ ተከራክረዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ የሕግ አካል የሆነው ፍርድ ቤት በተካሄደው ክርክር ፕ/ር ማልኮም ሻው፣ እስራኤል ላይ እነዚህ ክሶች መቅረብ እንደማይችሉ ተናግረዋል።

“ደቡብ አፍሪካ ለሐማስ ድጋፍ እየሰጠች ነው” ብለዋል።

በጋዛ የዘር ጭፍጨፋ ተፈጽሟል የሚለው ላይ ብይን ለመስጠት ፍርድ ቤቱ ዓመታት ሊወስድበት ይችላል።

ደቡብ አፍሪካ ማስረጃዎች ማቅረብም አለባት።

የዘር ጭፍጨፋ ተፈጽሟል የሚለውን በፍርድ ቤት ለማስወሰን ቀላል አይደለም።

የእስራኤል መከላከያ አላማው ምንድን ነው የሚለውን የሚያሳይ ጠንካራ ማስረጃ ማቅረብ ያስፈልጋል።

ይህም ተከታታይ እርምጃዎች መካከል ያለን አንድንት ማሳየትም ይጠይቃል።

እስራኤል የዘር ማጽዳት ፈጽማለት ወይም የጦር ወንጀል ተፈጽሟል የሚለውን ሳይሆን ፍርድ ቤቱ የሚመለከተው የዘር ጭፍጨፋ ክስን ነው።

ፍልስጤማውያን እየደረሰባቸው ያለውን ከማሳየት በዘለለ ከጋዛ 1% ነዋሪዎች መገደላቸውን መነሻ አድርጎ፣ የእስራኤል ግብ ፍልስጤማውያንን እንደ ሕዝብ በከፊል ወይም በአጠቃላይ የማጥፋት ነው የሚለውን ለፍርድ ቤቱ ማሳየት ይጠበቃል።

ደቡብ አፍሪካ ዘጠኝ ሊወሰዱ የሚችሉ እርምጃዎች ነው በ84 ገጽ ያቀረበችው።

እነዚህም በቀጣይ “የፍልስጤማውያንን ሕይወት ለመጠበቅ የሚውሉ” ተብለው ቀርበዋል።

የመጀመሪያው እስራኤል በጋዛ የምታደርገውን ድብደባ እንድታቆም ነው የሚጠይቀው።

ይህ እስራኤል ግቤን መትቻለሁ ከምትልበት ጊዜ ቀድሞ የሚፈጸም ሊሆን ይችላል።

እስራኤል በዚህ ረገድ የተከራከረችው እስራኤል እርምጃ እንዳትወስድ አግዶ ሐማስ እርምጃ እንዲወስድ የሚፈቅድ የሕግ ማዕቀፍ የለም ነው።

እስራኤል ፍርድ ቤቱ ለአገሪቱ የተዛባ ምልከታ እንዳለው ነው የምታምነው።

እስራኤል በጋዛ እየፈጸመች ያለውን ከፍተኛ ድብደባ እንድታቆም ዓለም አቀፍ ጫና እየበረታ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱ የውሳኔ ሐሳብ ካሳለፈ ጫናው የበለጠ ይጠነክራል።

ፍርድ ቤቱ ውሳኔን የማስፈጸም ኃይል የለውም። ስለዚህም ውሳኔውን እስራኤል ችላ ልትል ትችላለች።