January 13, 2024  – Konjit Sitotaw 

የብልፅግናው ኮሎኔል ተገደለ። በሠከላ እና በቲሊሊ ፋኖዎች በተደረገ የተቀናጀ ርምጃ ከፍተኛ ድል ተመዝግቧል።

በኮሎኔል አደመ ልጃለም፣ በሻለቃ እንደሻው ጌታነህ እንዲሁም በሺ አለቃ መለሠ የሻለም የሚመራው የሠከላ ፋኖ ጊዮን ብርጌድ እና በሻለቃ በላይ አሰፋ፣ በም/ሻለቃ መዝገብ መኩሪያ የሚመራው የቲሊሊ ፋኖ ዘንገና ብርጌድ የአሸባሪው የኦሮሙማ የብልፅግና ቡድን ከኮሶበር ለስብሰባ አመራሮችን ጭኖ ወደ ቲሊሊ ሲያዘግም እነዚያን ለመቀበል ከቡሬ በመነሳት ወደ ቲሊሊ ሲያዘግም ጀግኖቹ የሠከላ ፋኖዎችና የቲሊሊ ፋኖዎች ዘንገና ብርጌድ በጋራ ጥምረት በወሠዱት ርምጃ የአሸባሪው ቡድን ብዙ ሟችና ስፍር ቁጥጥር የሌለው ቁስለኛን ያስተናገደ ሲሆን አንድ የብልፅግና ኮሎኔል 73ኛ ክፍለ ጦር አመራርም ሊገደል ችሏል። የሠከላ ፋኖ የጊዮኑ አንበሳ ድል ተቀናጅቶ በዋለበት ውጊያ፣ የቲሊሊ አናብስቶች ገነው በዋሉበት ድል የኦሮሙማውን አሽከር አንገት ያስደፋ ታላቅ ድል ሆኖ ተመዝግቧል።

በጎጃም እዝ አዛዥ ሻለቃ ዝናቡ ልንገረው በታዘዘ የዲሽቃ መሳሪያ የተንኮታኮተው የብልፅግና ቡድን እግሬ አውጭኝ በማለት ሊፈረጥጥ ችሏል። የፋኖ ዱላ የከበደው አሸባሪው ቡድን በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሠ ፣ የህዝቡን ንብረት እየዘረፈ፣ ነዳጅ ሳይቀር ከማደያዎች እየቀማ ይገኛል።