By Wondimu Mekonnen

npdtsSooreatl1uAt cui Mil600 Ja470y:188a9r2gf7002ii7 2c124na 
በጠዋቱ፥ ከጓደኛዬ ከGirma Bekele የተላከልኝ ስጦታ፣! ———————–#Gojam_ልፃፍ ስለ ጎጃም _ ለትውልድ ሀገሬ ፣ከ’ማሆይ ገላነሽ _ ቅኔን ተበድሬ ፣ዜማውን ተውሼ _ ከአድማሱ ጀምበሬ ፣ከሐዲስ አለማየሁ _ ቃላትን ቆጥሬ ፣ካ’ባኮስትር በላይ _ ጀግንነት ተምሬ፥አትነካኩኝ ልፃፍ _ በግጥም ዘርዝሬ!መሸንቲ ቢኮሎ _ ዱርቤቴ ይስማላ ፣ዘንዘልማ አዴት _ መራዊ ሰከላ ፣እጅግ ይጣፍጣል _ እሸቱ ሲበላ!ቲሊሊ ኮሶበር _ ቻግኒ እንጅባራ ፣የሚገበይበት __ የፍቅር እንጀራ!ቢቡኝ ድጎ ፅዮን _ ቋሪት ደጋ ዳሞት፣መለያቸው ድፍረት _ አርማቸው ጀግንነት!እነሴና እነብሴ _ ደጄንና አቸፈር ፣ሸበልና ማርቆስ _ ዳንግላ ባህርዳር ፣የማርና ቅቤ _ የማኛ ጤፍ ምድር ፣እንዴት ብዬ ላውራው _ አያልቅም ቢነገር!ልፃፍ ስለ ጎጃም _ በብጣሽ ወረቀት፣ከአቡነ ቴዎፍሎስ _ እንዳገኝ በረከት፣ከእምቢ አልወለድም.. ከአቤ ጉበኛ………..እንድቀስም እውቀት!ከበውቀቱ _ ከአለቃ አያሌው፣ከኤፍሬም ታምሩ _ ከጂጂ ሽባባው፣ከአያልነህ ሙላቱ _ ጌትነት እንየው፤ከእነዚህ በሙሉ _ ጥበብ እንድቀዳ፣ልፃፍ ስለጎጃም _ ጠዋት በማለዳ!ማርቁማ ወይንማ _ ሽንዲ ወንበርማ ፣የምርት ጎተራ _ የሰብል አውድማ!ሞጣ ቀራኒዮ _ ቢቸና ደብረወርቅ ፣ልባቸው ሩህሩህ _ ፍቅራቸው የማያልቅ!አነደድ የጁቬ _ ሉማሜ ጎዛምን ፣የውቦች ቀዬ ነው _ ያስንቃሉ አለምን!አማኑኤል ደምበጫ _ ጃቢጠህናን ቡሬ ፣ጎጃም ውበት አለው _ ለምለም ነው ሀገሬ ።አንቺ የኔ ፍቅር. ……………….!ውሃ ትወጃለሽ _ ሰማሁልሽ ወሬ ፣ተዘጋጅ ላሳይሽ _ ምን ጎድሎት ሀገሬ!ወንዝ ከተመቸሽ ……………….!ከአባይ ከምንጩ _ ግዮን ከጠበሉ ፣ጨሞጋና ፈጣም _ ጎጃም ከመሀሉ ፣አብያና ጥጃን _ ብርና ላህ አሉ ፣ጉማራና ተምጫም _ ላንቺ ይበቃሉ ፣መዋኘት ካማረሽ …………….!ባህረ ጊዮርጊስ _ ገራይ ነው? ዘንገና ፣ወይስ ከጉደራ _ አልያ ከጣና ፣የትኛው ሐይቅ ላይ _ ምረጭ እንዝናና ፣ፍቅሬ ይህ ነው በይኝ _ ልውሰድሽ ልምጣና!ገዳምም ከፈለግሽ ………………!ሰኞ ጫቢ ማርያም _ ማክሰኞ ዋሸራ ፣ሮብ ደብረ ዲማ _ ሐሙስ ከድንግራ ፣አስጎበኝሻለሁ __ አቅፌሽ ኤሊያስን!አርብና ቅዳሜ _ ቢቸና ጊዮርጊስ ፣ናዳ ላይ ተሳልመሽ _ እሑድ ጣና ቂርቆስ፣ነይና ከጎጃም _ መንፈስሽ ይታደስ!ይሄው እንዳየሽው. ……………….!ህዝቡ ያስደምማል _ በደንብ ላስተዋለው፣ሲነጋገር በአሽሙር _ ቅኔና ዜማ አለው!ቡዳ ነህ አትበይኝ ………..!ቡዳ መንፈስ ሳይሆን _ የሚያምር ፍቅር ነው፣በጎጃሜ ቋንቋ _ ቡዳነት መውደድ ነው፣እምጥንተ ፍጥረት _ ከአዳም የወረስነው!ጎጃም ህቡዕ ነው. ………………!ጎጃም ምስጢር ነው. …………..!ጎጃም ምሉዕ ነው _ አያልቅም ቢነገር፣የጮቄ ተራራ __ አራት መከራክር ፣የብር አዳማ ጫፍ _ የአራራት አሳንሱር፣የአቮላ አቀማመጥ _ የአባ ዳሞ ታምር!በጋራ ሸንተረር _ የተዥጎረጎረች ፣ጢስ አባይ ፏፏቴን _ በእቅፏ የያዘች ፣ጎጃም ሙሽራ ናት _ በጌጥ የደመቀች!ይገለጥ መጽሐፉ _ ኦሪት ዘ’ፍጥረት ፣የሰው ልጅ እስትንፋስ _ የግዮን እናት ፣መሆኗን ያሳያል _ ጎጃም’ ገነት!!ከ#©facebook@sami የተወሰደ#ከወደዱት_ለጓደኛዎ_ያጋሩ#ደግሞ_ጎጃሜነኝ_ስልህ_በምክንያት_ነው#❤Gojam❤!
All reactions