January 16, 2024 

የተለያየ አገዛዝና መንግስት አይፀናም::

=========================

ድሮም ሆድ አደርነት ሊያስማማ አይችልም::

በጎጃም የፀጥታ መዋቅሩና የብልፅግና ካድሬዎች በግምገማ ተጋጭተው ስብሰባው መበተኑን የአካባቢው ምንጮች ገለፁ::

በአማራ ክልል የጸጥታ አመራሮችን አቅም ለመገንባት በሚል በደብረማርቆስ ከተማ የተጀመረው የሥልጠና መድረክ በብጥብጥና ባለመግባባት ተበትኗል::

የምሥራቅ ዕዝ አዛዥና የጎጃም ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ተብየውና የብርሃኑ ጁላ ተላላኪው ሌተናል ጀነራል መሐመድ ተሰማና የክልሉ የብልፅግና ከፍተኛ ምስለኔ ዶር ድረስ ሳህሉ ከመድረኩ በገጠማቸው ተቃውሞ አለመስማማት በመፈጠሩ ስብሰባው ተበትኗል::

እስከ ጥር 13 ይቆያል ተብሎ የነበረው የሥልጠና እና ግምገማ መድረክ ላይ በስም ብቻ ያሉት የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደርን ጨምሮ ከምሥራቅ ጎጃም፣ ከምዕራብ ጎጃም፣ ከሰሜን ጎጃም፣ ከአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር እንዲሁም ከባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር የተውጣጡ የብልፅግና የጸጥታ ኃይል አባላት ተሳታፊ ነበሩ:::ስብሰባው በፖሊስ ኮሌጅ ውስጥ እየተካሄደ ነበር:: የብጥብጡን መንስዔ እያጣራሁ ነው:: ( ምናላቸው ስማቸው )

Image