ግብፅ ከታላቁ የ’#ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ራሷን ማግለሏን ይፋ ማድረጓን ተከትሎ፣ ከግድቡ ጋር በተያያዘ ፍላጎቷን ለማሳካት በማሰብ፣ ኢትዮጵያን ዙሪያዋን በመክበብ ከጎረቤቶቿ ጋር የጦር ስምምነቶችን እያደረገች ትገኛለች።

ደቡብ ሱዳን እና ግብጽ ወታደራዊ ትብብራቸውን ለማጠናከር የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ተፈራረሙ።
ሁለቱ ሀገራት የምግባቢያ ሰነዱን የተፈራረሙት የደቡብ ሱዳን መከላከያ ሚኒስትር ቾል ቶን ባሎክ በግብጽ ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ ነው።
የደቡብ ሱዳን የኢንፎርሜሽን ሚኒስትሩ ሚካኤል ማኩዪ ሉት የወታደራዊ የትብብር ስምምነቱ በቅርቡ ተግባራዊ ይሆናል ብለዋል። “የመግባቢያ ሰነዱን የግብጽ መከላከያ ሚኒስትር ወደ ደቡብ ሱዳን በማምራት ተግባራዊ መደረግ ይጀመራል” ብለዋል።
ሚኒስትሩ፣ ደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት በሀገሪቱ ላይ በጣለው የጦር መሳሪያ ማዕቀብ ምክንያት መሳሪያ ለመግዛት ምንም አይነት ጥያቄም ሆነ ማመልከቻ ባታቀርብም፤ ከግብጸ ጋር በወታደራዊ ትብብር ለመስራት ከስምምነት ላይ መድርሷ በእጅጉ ተጠቃሚ ያደርጋታል ሲሉ ገልጸዋል።