የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አደጋ ደረሰበት – ቀላል ጉዳት
የተወሰኑ ተጓዦች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

መነሻው አዲስአበባ በማድረግ ወደ መቐለ ጉዞ ላይ የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አደጋ ደረሰበት። መንገደኞች አሳፍሮ ዛሬ ከቀኑ 6 ሰዓት 20 ከአዲስአበባ የተነሳው እና ኢቲ 106 በተባለ በረራ ወደ መቐለ ጉዞ ላይ ሳለ በደረሰ “ድንገተኛ” በተባለ የቴክኒክ ችግር አደጋው መከሰቱ ተገልጿል።
አውሮፕላኑ መቐለ ሲደርስ ወድቆ የታየ ሲሆን፥ አሜሪካዊ ዜግነት ያላቸው አንድ መንገደኛ ጨምሮ በተወሰኑ ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።
ገብረህይወት ወልደገብርኤል የተባሉ አንድ መንገደኛ “አውሮፕላኑ አደጋ እንደደረሰበት የተነገረን ከአዲስአበባ እንደተነሳን ወድያዉኑ ነበር” ብለዋል።
” የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ ምርመራ እየተደረገ ይገኛል ” – የኢትዮጵያ አየር መንገድ

መነሻውን አዲስ አበባ ያደረገ የበረራ ቁጥሩ ” ኢቲ106 ” የሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞች አውሮፕላን በመቐለ ” አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ” አደጋ እንዳጋጠመው ይታወቃል።
ይህ በተመለከተ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምን አለ ?
– የአውሮፕላኑ በረራ ቁጥር ET106/18 ነው።
– ከአዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት የተነሳው ቀን 6:30 ላይ ነው።
– ክስተቱ ያጋጠመው በአሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ከቀኑ 8 ስአት አካባቢ ነው። በሚያርፍበት ወቅት ከመንደርደሪያው መንገድ ተንሸራቶ ወጥቷል።
– ሁሉም ተሳፋሪዎችና የበረራ ቡድን አባላት ጉዳት ሳይደርስባቸው በሰላም ወጥተዋል።
– አደጋው እንዴት ሊፈጠር እንደቻለ / የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ ምርመራ እየተደረገ ይገኛል።
የኢትዮጵያ በተፈጠረው ችግር መጉላላት ለደረሰባቸው መንገደኞችም #ይቅርታ ጠይቋል።