ፕሪሚር ሊግ

ከ 6 ሰአት በፊት

ኤቨርተን እና ኖቲንግሃም ፎረስት የፕሪሚር ሊጉን የፋይናንስ ሕጎች ጥሰዋል በሚል አዲስ ክስ ተመስርቶባቸዋል።

ኤቨርተን ከዚህ ቀደም በቀረበበት ክስ 10 ነጥብ ተቀንሶበት ይግባኝ ጠይቋል። ቢቢሲ በጉዳዩ ዙሪያ ሚነሱ ጥያቄዎችን እንደሚከተለው ተመልክቷቸዋል።

ፕሪሚየር ሊጉ ሲጠናቀቅ ምን ሊፈጠር ይችላል?

እነዚህ አዳዲስ የፕሪሚየር ሊጉ ጉዳዮች ከወራት በኋላ የሚታዩ ይሆናል።

የኤቨርተን ጉዳይ ግን የሚታየው ከዚህ በፊት ክለቡ ላይ በተላለፈው ቅጣት ዙሪያ ቀረበው ይግባኝ ከተሰማ በኋላ ነው።

እነዚህ ጉዳዮች በሚታዩበት ወቅት ወራጅ ቡድኖች ተለይተው ያለመታወቃቸው ዕደል ሰፊ ነው።

ውሳኔ ቢተላለፍም ቡድኖች ይግባኝ መጠየቃቸው አይቀርም። ይግባኙ የሚሰማው ውድድሩ ከተጠናቀቀ በኋላ የመሆን እድሉ ስለሚሰፋ በውድድሩ ላይ ምስቅልቅል መፍጠሩ አይቀርም።

በርንሌይ ከኖቲንግሃም ፎረስት እና ኖቲንግሃም ፎረስት ከአርሰናል የሚያደርጓቸው የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታዎችስ?

ከመርሃ ግብር አንጻር እነዚህ ጨዋታዎች የሊጉ የፍጻሜ ጨዋታዎች መሆናቸው እሙን ነው። ከህግ አንጻር ግን የ2023/24 የውድድር ዘመን ዓመታዊው ጠቅላላ ጉባኤ ሰኔ ውስጥ ተከናውኖ የወረዱ ቡድኖች ሰርተፊኬታቸውን አስኪቀይሩ ድረስ ሊጉ ፍጻሜ አግኝቷል አይባልም።

በዚህ ወቅት ነው ሁሉም ነገር የሚወሰነው።

ምን ዓይነት ሕጎች ተጣሱ?

የትርፍ እና ዘላቂነት ሕጎች (ፒኤስአር) ዓላማ በፕሪሚየር ሊግ ውስጥ የፋይናንስ መረጋጋትን ለመፍጠር ነው።

በ2015/16 ውድድር ዘመን ነው ተግበራዊ የተደረጉት። ክለቦችን ከአቅም በላይ ወጪ የመጠበቅ ጉዳይ ቀደም ሲልም የነበረ ነው።

ፖርትስማውዝ ያለበትን የ60 ሚሊዮን ፓውንድ ዕዳ ለመክፈል አዲስ ገዢ ባለማግኘቱ እአአ በ 2010 እርምጃ የተወሰደበት የመጀመሪያው ክለብ ለመሆን ችሏል።

አሁን ያሉት ሕጎች ለክለቦች የሚፈቀደውን ኪሳራ ይገድባሉ። ይህ ኪሳራ መጠን ግን በባለቤቶቹ በሚደረግ የገንዘብ ድጋፍ ሊጨምር ይችላል።

ሕጎቹ ግን መቀየር አለባቸው። ልክ እንደ አውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ሁሉ ወጪን ከትርፍ ጋር የሚያመጣጥን ነው።

ደንቦቹን የሚቃወሙት ከቱጃር ባለቤቶች የሚደረግን የገንዘብ ፍሰት የሚገደብ ሲሉ ይቃመወሙታል። ይህ ትልልቆቹ ክለቦች በጣም ሃብታም እና ስኬታማ ሆነው እንዲቀጥሉ የሚደረግ ሙግት ነው።

ክለቦች ምን ያህል እንዲያወጡ ተፈቅዶላቸዋል?

በዋናነት ክለቦች በሦስት ዓመት ሪፖርታቸው የተዘዋወረ 105 ሚሊየን ፓውንድ ድረስ ኪሳራ ተፈቅዶላቸዋል።

ሕጎቹ በኮቪድ ወረርሽኙ ወቅት በትንሹ ላላ ተደርገው ነበር። ይህ ሕግ ክለቦች እንደ አካዳሚ ባሉት ላይ የሚያደርጉትን ኢንቨስትመንት የሚመለከት አይደለም።

‘በክለቡ ያደጉ’ ተጫዋቾችን መሸጥ በነጻ የተገኘን ተጫዋች ከመሸጠ የበለጠ ተጽእኖ አለው። ማንቸስተር ሲቲ በክረምቱ ኮል ፓልመርን ለቼልሲ በ40 ሚሊዮን ፓውንድ የሸጠበት ለዚህ ማሳያ ነው።

ለመወዳደር በሚሞክሩ ክለቦች ላይ ህጎቹ ምን ተጽእኖ አላቸው?

ኒውካስል እና አስቶንቪላ ትልልቅ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ናቸው። ትልቅ ታሪክ ያላቸው እና በከበርቴ ባለቤቶች ተይዘው እስከ ስድስት ያለውን ደረጃ ለመያዝ እየታገሉ ነው።

ሁለቱም ቡድኖች በርካታ ተጫዋቾችን ወደ ቡድናቸው ለማምጣት አንዲችሉ አንድ ኮከብ ተጫዋቻቸውን ሊለቁ ፈቃደኛ ሊሆኑ እንደሚችሉ በቅርቡ ተናግረዋል።

ኒውካስል የቅርብ ጊዜውን ገቢውን ይፋ ባደረገበት ወቅት ንግግር ያደረጉት ዋና ሥራ አስፈፃሚው ዳረን ኢሌስ የማግፒዎቹ ገቢ ወደ 250 ሚሊዮን ፓውንድ መሆኑን ጠቁመዋል።

ቶተንሃም ያገኘው ገቢ 440 ሚሊዮን ፓውንድ ነው።

ዘንድሮ ምን ተለወጠ? ምን ዓይነት ለውጦችስ ይጠበቃሉ?

ኤቨርተን በመጋቢት 2023 የትርፍ እና የዘላቂነት ሕጎችን ጥሷል በሚል ክስ ቀርቦበታል። ጉዳዩ ባለፈው ጥቅምት ታይቷል።

ህዳር ላይ 10 ነጥብ ተቀነሰበት። ክለቡ ቅጣቱን በመቃወም ይግባኝ ጠይቋል።

ክለቡ ጥሰቱን ፈጽሟል በተባለበት ወቅት መውረድ አደጋ ያንዣበባቸው ኖቲንግሃም ፎረስት፣ ሳውዝሃምፕተን፣ ሊድስ እና ሌስተር እንዲሁም በወቅቱ የወረደው በርንሌይ ቅጣጡ የተላለፈው ሕጉ በተጣሰበት ውድድር ዓመት ላይ አልተላፈም በሚል ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስዱ አስጠንቅቀው ነበር።

ለዚህም ምላሽ ሰጠው ፕሪሚየር ሊጉ አዳዲስ ህጎችን ተግባራዊ አድርጓል። ይህም ሕግ ክለቦች የትርፍ እና የዘላቂነት መረጃቸውን ቀደም ብለው እንዲያስገቡ ወስኗል።

የወደፊት የሚደረጉ ለውጦች ስለመኖራቸው ባይረጋገጠም ከአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር የፋይናንሻል ኤይር ፕሌይ (ኤፍኤፍፒ) ጋር አብረው መሄድ አለባቸው።

ይህም ክለቦች ከገቢያቸው 70 በመቶ የሚሆነውን ለደመወዝ፣ ለዝውውር እና ለወኪሎች ክፍያ እንዲያውሉት ይፈቅድላቸዋል።

ክለቦች ነጥብ ይቀነስባቸው ይሆን?

ከማስጠንቀቂያ እስከ ነጥብ መቀነስ ይደርሳል። ኤቨርተን የ10 ነጥብ ቅጣት የተላለፈበት 19.5 ሚሊዮን ፓወንድ ተላልፎ በመገኘቱ ነው። ለዚህም ነው ክለቦች ወጪያቸውን በተፈቀደላቸው ልክ ለማውጣት የሚጥሩት።

ኤቨርተኖች ከተፈቀደላቸው በላይ ወጪ ማድረጋቸውን አምነዋል። ይህ የተፈጠረበትን ስድስት ምክንያቶችን አስቀምጠዋል።

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የተጫዋቾቻቸውን ዋጋ በመቀነሱ እና እነሱን በመሸጥ ሊያገኙት የሚችሉትን መጠን መቀነሱ ተጠቃሶች ናቸው። ቀሪዎቹ አምስት ምክንያቶች ውድቅ ሆነዋል።

ማንቸስተር ሲቲስ?

የትርፍ እና የዘላቂነት የተመለከተ ክስ ሲቀርብ አንዳንድ የእግር ኳስ ደጋፊዎች ‘ማንቸስተር ሲቲስ?’ ይላሉ።

ሲቲ ከ2009 ጀምሮ የካቲት 2023 ላይ ከወጪያቸው ጋር በተያያዙ ከ100 ጥሰቶች ፈጽመዋል በሚል ክስ ተመስርቶባቸዋል።

ይህም ድብቅ ክፍያዎችን እና አለመተባበርን ያጠቃልላል። እስከ 2024-25 የውድድር ዘመን መጨረሻ ድረስ መፍትሔ ይኖራል ተብሎ አይታሰብም።

እነዚህ ለብዙ ዓመታት የተንከባለሉ እና ጥያቄ የሚነሳባቸው ክሶች በመሆናቸው እንደቅርብ ጊዜዎቹ ቀላል አይደሉም። የክርክሮቹ ዋነኛ ጉዳይ ከመጠን በላይ ወጪ ላይ ወይም ገቢ ልዩነቶች ላይ ያተኮሩ ናቸው።

ቼልሲስ?

አንዳንድ መላምቶች ቢኖሩም ላለፉት 18 ወራት ለዝውውሮች ከፍተኛ ወጪዎችን አድርገውም ቼልሲዎች ህጉን እንዳከበሩ ያምናሉ።

ሰማያዊዎቹ ለተጫዋቾች ግዢ አንድ ቢሊዮን ፓውንድ ቢያወጡም አካሄዳቸው የፕሪምየር ሊጉን የዝውውር መልክ ለውጦታል።

ለተጫዋቾች ረዥም ኮንትራት ይሰጣሉ። ለምሳሌ ኤንዞ ፈርናንዴዝን በ106 ሚሊዮን ፓውንድ ካዘዋወሩ በኋላ የስምንት ዓመት ውል በማስፈረማቸው ክፍያው ለእነዚህ ዓመታት እንዲራዘም አድርገዋል።

ይህ ታክቲክ አሞርታይ ዜሽን የሚባል ሲሆን ቼልሲዎች ይህንኑ አካሄድ በርካታ ተጫዋቾችን ለማስፈረም ከተጠቀሙ በኋላ የሊጉ ክለቦች የተጫዋቾች የዝውውር ወጪ ክፍያ በአምስት ዓመት እንዲገደብ ድምጽ ሰጥተዋል።

ቼልሲዎች ከተጫዋች ሽያጭ ያገኙትን 450 ሚሊየን ፓውንድም ያነሳሉ። ክለቡ ያሳደጋቸውን እንደ ሩበን ሎፍተስ ቺክ እና ሜሰን ማውንትን በመሸጥ እንደ ሉዊስ ሆል ያሉትን በውሰት በመስጠት ከፍተኛ መጠን ያለው ‘ንጹህ ትርፍ’ እንዲያስመዘግቡ አስችሏቸዋል።

ክለቡ የተወሰነ ገንዘብ ማግኘት ከፈለገ ኮኖር ጋላገርን፣ ኢያን ማትሰንን እና አርማንዶ ብሮጃን የመሸጥ አማራጭ አለው።

ቼልሲዎች ከቀድሞው የክለቡ ባለቤት ሮማን አብራሞቪች ጋር የተገናኙ ክፍያዎች ላይ ተጨማሪ ምርመራ ሊደረግበት ይችላል።

የእግር ኳስ ማህበሩ እና ፕሪሚየር ሊጉ በምርመራ ላይ ሲሆኑ ከ2012 እስከ 2019 “ያልተሟላ የፋይናንስ መረጃ አቅርበዋል” በሚል ዩኤፋ ቅጣት አስተላልፎባቸዋል።