
20 ጥር 2024, 09:24 EAT
በማዕከላዊ ቻይና የትምህርት ቤት ማደሪያ ውስጥ እሳት መነሳቱን ተከትሎ 13 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ።
የቻይና ብሔራዊ ጣቢያ ዢንዋ እንደዘገበው ትናንት ምሽት ላይ ነው እሳቱ የተነሳው።
በሄናን ግዛት ያንሺፑ መንደር በሚገኝ የአዳጊዎች ትምህርት ቤት ውስጥ ነበር ክስተቱ።
የግል ትምህርት ቤቱ የህጻናት መዋያ እና የመጀመሪያ ደረጃ ነው። ኃላፊው በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተደረገም ነው።
አንድ ተጨማሪ ሰው ለሕክምና ሆስፒታል ተወስዷል።
ስለሞቱት ሰዎችና ስለ እሳቱ መንስኤ ተጨማሪ መረጃዎች አልወጡም።
ዢንዋ እንዳለው እሳቱ በተነሳ በአንድ ሰዓት ውስጥ ማጥፋት ተችሏል።
በቻይና የሕንጻና ግንባታ ቁጥጥር ትግበራ እምብዛም ስላልሆነ እሳት በተደጋጋሚ ይነሳል።
ያለፈው ጥቅምት በሉሊንግ ከተማ በሚገኝ ቢሮ ውስጥ እሳት ተነስቶ 26 ሰዎች ሞተዋል።
- የሥነ ዜጋ እና ሥነ ምግባር ትምህርት ከ12ተኛ ክፍል ፈተናዎች መካከል እንዲወጣ ተደረገ20 ጥር 2024
- ጋዛ፡ ‘ማቆሚያ ያጣው ጦርነት ሕይወታችንን አመሳቀለው’20 ጥር 2024
- “ዓላማዬ የኢትዮጵያ የሀገረ-ሰብ ሙዚቃ መሳሪያዎችን ማጉላት ነው”- አስቻለው ፈጠነ20 ጥር 2024
ከዚያ በፊት ደግሚ በመዲናዋ ቤጂንግ ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል በተነሳ እሳት 29 ሰዎች ሞተዋል። አብዛኞቹ ሟቾች ሕሙማን ነበሩ።
የእሳት አደጋውን ተከትሎ በተደረገ ምርመራ 12 ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል።
ከአደጋው በኋላ የወጡ ምሥሎች እንደሚያሳዩት ሰዎች ሕይወታቸውን ለማዳን በመስኮት ለመዝለል ሲሞክሩ ነበር።