January 21, 2024 

The Ethiopian Air Force has acquired an undisclosed number of Akinci unmanned aerial vehicles (UAVs) from Turkey and Russian-made Sukhoi Su-30 fighter jets.

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ሰሞኑን የተረከባቸው ሩሲያ ሠራሽ ሱ-30 ተዋጊ ጄቶች ሕንድ ለሩሲያ ተመላሽ ያደረገቻቸው ሊኾኑ እንደሚችሉ አንዳንድ ዓለማቀፍ ወታደራዊ ድረገጾች ዘግበዋል።

The Sukhoi Su-30 is a twin-engine fighter aircraft first introduced in Russia in 1992 as an air superiority and strike fighter.Its main roles include all-weather air interdiction and long-range strike operations, utilizing anti-air and surface missiles weighing up to 8,000 kilograms (17,600 pounds). The fighter jets are believed to be part of an 18-unit batch manufactured for the Indian Air Force and delivered between 1997 and 1999.The acquisition makes Ethiopia the fourth African nation to operate the Russian-made jets, following Algeria, Angola, and Uganda.

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ሰሞኑን በግዢ የተረካባቸው ኹለቱን ሱ-30 ተዋጊ ጄቶች እንደኾነ የጠቆሙት ዘገባዎቹ፣ ምናልባት ቁጥሩ ከዚያ ከፍ ሊል እንደሚችል ጠቁመዋል።

ሕንድ ሱ-30 ተዋጊ ጄቶችን ከተገለገለችባቸው በኋላ ለሩሲያ የመለሰቻቸው፣ እኤአ በ2008 ገደማ እንደነበርና ሌላ ገዢ እስኪገኝ ሩሲያ ያለ አገልግሎት አስቀምጣቸው እንደቆየች ዘገባዎቹ አመልክተዋል።

ሕንድ ተመላሽ ካደረገቻቸው 18 ሱ-30 ተዋጊ ጄቶች መካከል፣ 12ቱን አንጎላ ከአምስት ዓመት ገደማ በፊት በግዢ እንደተረከበቻቸው ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል፣ ስንት ሱ-30 ተዋጊ ጄቶችን እንደተረከበና ከየት አገር እንደተገዙ በወቅቱ አልገለጠም።

Source :  https://www.thedefensepost.com/2024/01/19/ethiopia-akinci-uav-sukhoi/