January 21, 2024 – Konjit Sitotaw 

(ኢትዮ 360 – ጥር 12/2016) በአዲስ አበባ ከተማ የጥምቀት በአልን ሲመሩና በጭፈራ ሲያጅቡ የነበሩ ወጣቶች በገፍ ሊታፈሱ መሆኑን የኢትዮ 360 የውስጥ ምንጮች አጋለጡ።

ወጣቶቹ በገፍ የሚታፈሱትም ከሰው በላው መሪ በወረደ ትእዛዝና አዳነች አበቤ ባሰለጠነቻቸው ባንዳዎች አማካኝነት ምስላቸው እንዲቀረጽ በመደረጉ ነው ብለዋል።

ይሄ የተሰማራው የባንዳው ስብስብም ምስሎቹን ከቀረጸ በሁዋላ በቀጥታ ለኦህዴዱ የደህንነት መስሪያ ቤት እያደረስ መሆኑንም አስታውቀዋል።

በተለይ ደግሞ በዋናነት ትኩረት የተደረገባቸው መገናኛና ጊዮርጊስ አካባቢ ያሉ የበአሉ አክባሪ ወጣቶች መሆናቸውንም ጠቁመዋል።

በቀጣይ ቀናትም በተከታታይ አፈናው እንዲካሄድ ትእዛዝ መውረዱንም የኢትዮ 360 የውስጥ ምንጮች አጋልጠዋል።

ትእዛዙ ወጣቶቹ በተገኙበት ቦታ ሁሉ እንዲያዙ የሚል መመሪያ ማካተቱንም ጨምረው ገልጸዋል።