January 27, 2024 – Konjit Sitotaw

ብሄራዊ ባንክ በቅርቡ የቀረጸው የሦስት ዓመት ስትራቴጂ፣ በሦስት ዓመታት ውስጥ የውጭ ምንዛሬ ክምችቱን በሦስት ዕጥፍ ለማሳደግና ለኹለት ወራት ከግማሽ ሸቀጦችን ከውጭ ለማስገባት የሚበቃ መኾኑን ሪፖርተር አስነብቧል።

ባንኩ እስከተያዘው በጀት ዓመት መጨረሻ ብቻ ላንድ ወር ሸቀጦችን ለማስገባት የሚበቃ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ክምችት ለመያዝ እንዳቀደ ዘገባው ጠቅሷል።

ባንኩ ባኹኑ ወቅት ያለው የውጭ ምንዛሬ ክምችት ካንድ ወር ላነሰ ጊዜ ብቻ ሸቀጦችን ለማስገባት የሚበቃ ነው።

አንዱ የባንኩ ስትራቴጂ ግብ፣ በተያዘው በጀት ዓመት መገባደጃ ላይ የአገሪቱን የዋጋ ንረት ወደ 20 በመቶ ማውረድ እንደኾነ ዘገባው አመልክቷል።