January 27, 2024 –

የአፍሪካ ኅብረት ሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት ልዑካን ቡድን ዛሬ ወደ ትግራይ እንደሚያቀና ይጠበቃል።

ልዑካን ቡድኑ ዛሬና ነገ በሚያደርገው ጉብኝት በፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ባለሥልጣናትና መቀሌ ከተጠለሉ የጦርነቱ ተፈናቃዮች ጋር ለመወያየት ቀጠሮ ይዟል።

የምክር ቤቱ ልዑካን ቡድን ባለፈው ዓመት የካቲት በክልሉ ለማድረግ ያሰበው የመጀመሪያው ጉብኝት፣ የፌደራሉን መንግሥት ትብብር በማጣቱ ሳይሳካ መቅረቱ ይታወሳል።