January 27, 2024 – Konjit Sitotaw 

ኢትዮጵያ አባል የኾነችበት የምሥራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ጦር በአባል አገራት የሚከሰቱ ግጭቶችን ለማስቆም ለመሠማራት ዝግጁ መኾኑን አስታውቋል።

ጦሩ፣ ጥሪ ከተደረገለት፣ በሱዳንና በዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፐብሊክ ግጭቶችና የኢትዮጵያንና ሱማሊያን ውጥረት ለማርገብ ለመሠማራት ዝግጁነቱን ገልጧል።

የቀጠናው ተጠባባቂ ጦር የተውጣጣው፣ ኢትዮጵያንና ኬንያን ጨምሮ ከ10 አባል አገራት ነው።

ቀጠናዊው ጦር፣ በአባል አገራት የሰላም ማስከበርና ግጭት የመከላከል ተልዕኮዎች የመሠማራት ብቃት ላይ የደረሰው ከዘጠኝ ዓመታት በፊት ቢኾንም፣ እስካኹን ባንድም ተልዕኮ አልተሠማራም።