January 27, 2024 

ከገዢው ብልጽግና ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበርነታቸውና ከመንግሥት ሥልጣናቸው ትናንት የለቀቁት ደመቀ መኮንን ኢትዮጵያ የገጠሟትን የአገር ግንባታ ፈተናዎች ለማስተካከል ሕገመንግሥቱን ማሻሻል አንዱ ቀልፍ መፍትሄ እንደኾነ በስንብት ንግግራቸው ላይ ጠቁመዋል።

ደመቀ፣ በአገሪቱ የሚታዩት የሰላም እጦት፣ ሞትና መፈናቀል ልብ ሰባሪ መኾናቸውንም በንግግራቸው አውስተዋል።

የመልቀቂያ ጥያቄ ያቀረቡት ከዓመታት በፊት መኾኑን ጠቅሰው ጥያቄያቸው ተቀባይነት በማግኘቱ ደስታቸውን የገለጡት ደመቀ፣ በሥልጣን ዘመናቸው ላጎደሏቸው ነገሮች ይቅርታ ጠይቀዋል።