
በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በቦሰት ወረዳ ቤተ ክህነት የመርቆ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ባልታወቁ የታጠቁ ኃይሎች ተቃጥሏል፡፡
—————————————–
በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በቦሰት ወረዳ ቤተ ክህነት የመርቆ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን በአሳዛኝ ሁኔታ ባልታወቁ የታጠቁ ኃይሎች ትናንት ጥር 17/2016 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በግፍ ተቃጥሏል፡፡
የሚዲያ ክፍላችን ባገኘው መረጃ መሠረት በቦታው ላይ በተደጋጋሚ ጊዜ ዛቻና ማስፈራሪያ ሲያደርጉ የቆዩ ቢሆንም በትናንትናው ዕለት ሙሉ በሙሉ ንዋዬ ቅድሳቱ የተቃጠለ ሲሆን የቤተ መቅደሱ የውስጥና የውጭ ክፍል ጉዳት ያደረሰ ከፍተኛ ቃጠሎ አድርሰዋል፡፡ በጉዳዬ ላይ ሀገረ ስብከቱ አስፈላጊውን የማጣራት ሥራ እየሠራ ይገኛል፡፡
ለአካባቢው ኦርቶዶክሳውያን ይኼ ትልቅና ከባድ ቅስም የሚሰብር አስጸያፊ ድርጊት በመሆኑ የሚመለከተው አካል አስፈላጊ ጥበቃ ሊያደረግላቸው ይገባል እንላለን፡፡
ጥር 18/2016 ዓ.ም
ምንጭ፦ምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት!!!!