በኮሚሽኑ የአስቸኳይ ሙስና መከላከል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ገዛኸኝ ጋሻው
ዜና ሀብታቸውን ያላስመዘገቡ አራት ሺሕ የመንግሥት ኃላፊዎችና ሠራተኞች ተቀጥተው አስመዘገቡ
ቀን: January 28, 2024
- ሀብታቸውን ካስመዘገቡ 41 ከፍተኛ አመራሮች ትክክለኛ መረጃ የሰጠው አንዱ ብቻ ነው ተብሏል
ሀብታቸውን በፈቃደኝነት ለማስመዝገብ በተቀመጠላቸው ጊዜ ያላስመዘገቡ አራት ሺሕ የመንግሥት ኃላፊዎችና ሠራተኞች በቅጣት እንዲያስመዘግቡ ማድረጉን፣ የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ በቅጣቱም ከአራት ሚሊዮን ብር በላይ መገኘቱ ተጠቆሟል፡፡
ኮሚሽኑ ይህንን ያስታወቀው ዓርብ ጥር 17 ቀን 2016 ዓ.ም. በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡
ኮሚሽኑ እንዳስታወቀው ኃላፊዎቹና ሠራተኞቹ በሕግ የሚጠየቁ ሲሆን፣ ሙስናን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚካደሄው የሀብት ማስመዝገብ ሒደት ውስጥ ሀብታቸውን ባስመዘገቡ 41 የመንግሥት አመራሮች ላይ በተደረገው የትክክለኛነት ማጣራት አንድ አመራር ብቻ ትክክለኛ መረጃ ማቅረቡ ተገልጿል፡፡
በዚህም ከ41 የመንግሥት አመራሮች የምዝገባ ሰነድ መካካል የ24 ከፍተኛ፣ 16 የመካከለኛ ደረጃ የሚባሉ የሀብት ልዩነት ሲገኝበት የአንድ አመራር ብቻ በትክክል ተመዝግቦ መገኘቱን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡
በኮሚሽኑ የአስቸኳይ ሙስና መከላከል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ገዛኸኝ ጋሻው፣ በአገር አቀፍ ደረጃ በመንግሥት ተቋማት ውስጥ ከሚገኙ 2.3 ሚሊዮን መሠራተኞች ውስጥ 1.8 ሚሊዮን ያህሉ ሀብታቸውን አስመዝግበዋል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም ወደፊት ተጠያቂነትን የማረጋገጥ ሥራ እንደሚከናወን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ ከዚህ ቀደም ሀብትና ንብረታቸው ታግዶ ጉዳያቸው እየተጣራ ካሉ 45 አመራሮች ጋር አብሮ እንደሚታይ አስረድተዋል፡፡
የአገር ሀብት የበዘበዙ ግለሰቦች ተመጣጣኝ ቅጣት ማግኘት እንዳለባቸው የኮሚሽኑ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተስፋዬ ሻሜቦ ገልጸዋል፡፡
ኮሚሽኑ በ2016 ዓ.ም. ግማሽ ዓመት በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች፣ በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽኖች በግዥ፣ በመሬት፣ በሠራተኛ ቅጥር፣ በንብረት ማስወገድና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ አስቸኳይ ጥናት ማድረጉን አስታውቋል፡፡
በተሠራው አስቸኳይ የሙስና መከላከል በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች 678 ሚሊዮን ብር እና 8,490 ዶላር ከሙስና ምዝበራ ማዳን መቻሉን፣ እንዲሁም በክልሎችና በከተማ አስተዳደር ኮሚሽኖች በተሠራ 182 የአስቸኳይ የሙስና መከላከል ሥራ 323 ሚሊዮን ብር እና 68 ሺሕ ካሬ ሜትር የከተማ ቦታ፣ 21 ሚሊዮን ካሬ ሜትር የገጠር መሬት ለማዳን ተችሏል ተብሏል፡፡ ከልማት ተነሺዎች ጋር በተያያዘ በሙስና የተጠረጠሩ አካላት ጉዳያቸው እየታየ መሆኑ ተገልጿል፡፡
January 28, 2024