January 28, 2024 – Konjit Sitotaw
ህወሓት ለ41 ቀናት ፤ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዚደንት ከ64 ቀናት በላይ መካሄዱ የሚገልፁት ረጅም ስብሰባ ዛሬ መጠናቀቁ ፍንጭ ተሰጠ።
ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ ጥር 19/2016 ዓ.ም አመሻሽ ” ኢንስቲትዩት ግርዓልታ ንመፅናዕትን ስልጠናን ” ከትግራይ ህዝባዊ ግንኙነቶች ጉባኤ በመተባበር ባዘጋጀው የሁለት ቀን ውይይት ማጠቃለያ ተገኝተው እንዳሉት ድርጅታቸው ህወሓት ያካሄደው የግምገማ ፣ ሂስና ግለሂስ መድረክ ዛሬ መጠቃለሉን ፍንጭ ሰጥተዋል።
ፕረዚደንቱ ዛሬ በመድረኩ በመገኘት ባደረጉት ንግግር ስብሰባው መጠናቀቁን የሚመለከት ፍንጭ ሰጥተዋል።
በተሰብሳቢዎቹ መካከል መግባባት መደረሱን፣ ህዝቡን ወደ ተሻለ የለውጥ ጉዞ መምራት የሚችል ማስተካከያ መደረጉንም ተናግረዋል።
ፕረዚደንቱ ” ተደረሰ ” ስላሉት መግባባትና ማስተካካያ ዝርዝር መረጃ እንዳልሰጡ ከቦታው የዘገበው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።