
ከ 6 ሰአት በፊት
የአሜሪካ መንግስት፣ ባለፈው ዕሁድ ዮርዳኖስ ውስጥ በድሮን ጥቃት የተገደሉት ሶስት የአሜሪካ ወታደሮችን ማንነት ይፋ አድርጓል።
የ46 ዓመቱ ሃምሳ አለቃ ዊልያም ጄሮም ሪቨር፣ የ24 ዓመቷ ኬኔዲ ሌዶን ሰንድረስ እና የ23 ዓመት ዕድሜ ያለው ቤሮና ኤሌክስ አንድሪያ ሞፌት የሚኖሩበት ቤት በድሮን ከተመታ በኋላ ህይወታቸው አልፏል።
አሜሪካ ይህ ጥቃት ኢራን የምትደግፈው ሂዝቦላህ እንደፈጸመው ከሳለች። ፔንታገን ቡድኑ ላይ ክትትል እያደረገ እንደሆነ ጠቁሟል።
ፔንታገን አሜሪካ ከኢራን ጋር ጦርነት ውስጥ መግባት አትፈለግም ሲልም አክሏል።
“ጦርነት አንፈልግም ነገር ግን ኃይላችን ላይ ለተፈጸመው ጥቃት የአጸፋ ምላሽ እንሰጣለን” ብሏል ባወጣው መግለጫ።
ጥቃቱ የተፈጸመበት ድሮን ኢራን ሰራሽ እንደሆነ የአሜሪካ ባለስልጣናት በአሜሪካ ለሚገኘው የቢቢሲ አጋር ገልጸዋል።
ምንጮቹ ድሮኑ ሻዳ ተብለው የሚጠሩት የኢራን ድሮን ሲሆኑ አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውሉ ናቸው። እነዚህን ድሮኖች ኢራን ለሩስያ ሰጥታለች።
ሆኖም ኢራን ጥቃቱን ያደረሰው ወታደራዊ ቡድን ትደግፋለች መባሉን አስተባብላለች።
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተሸለሙት አግሪኮላ ሜዳሊያ ምንድን ነው? ለማንስ ይሰጣል?29 ጥር 2024
- የአፍሪካ ዋንጫ፡ አዘጋጇ አይቮሪ ኮስት ሴኔጋልን ጥላ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈችከ 7 ሰአት በፊት
- የዓለማችን ግዙፍ የጭነት መርከቦች እየሸሹት ያለው ቀይ ባሕርከ 8 ሰአት በፊት
ፔንታገን የተገደሉት ሶስት ወታደሮች፣ አሜሪካ ጆርጂያ ግዛት ከሚገኘው ተጠባባቂ ኃይል ወደ መካከለኛው ምስራቅ የተጓዙ እንደነበሩ አሳውቋል።
ባለፈው ዕሁድ በአሜሪካ ወታደሮች ላይ የተፈጸመው ጥቃት ከሶሪያ ደንብር አቅራቢያ በሚገኘው ሩክባን በተባለ የዮርዳኖስ አከባቢ ነው።
ስሙ ያልተገለጸ የአየር መቃወሚያ ስርዓት የወታደሮችን ቤት መምታቱን ተከትሎ ከ40 በላይ ወታደሮች ተጎድተዋል።
ጥቃቱ ሲደርስ በወታደራዊ ሰፈሩ የነበረው የአየር መቃወሚያ ስርዓት ጠፍቶ ነበር። ይህም የሆነው ጥቃት የፈጸመው ድሮን በደረሰበት ተመሳሳይ ሰዓት ሌላ የአሜሪካ ድሮን እየተመለሰ ስለነበር እንደሆነ ባለስልጠናት ገልጸዋል።
ኢራን ጥቃቱን ከዳረሰው ቡደን ጋር ግንኙነት የለኝም ስትል አስተባብላለች።
የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ናስር ካናኒ ሀገራቸው በጥቃቱ እንዳልተሳተፈች ገልጸው “አማጽያኑ ፍልስጠማውያንን ወይም የራሳቸውን ሀገር ለመከላከል በወሰዱት ውሳኔ ላይ አልተሳተፍንም” ብለዋል።
የኢራኑ የደህንነት ሚኒስትር ኢስማኤል ካቲብ ደግሞ ጥቃቱ ለአሜሪካ ጸብ አጫሪነት የተሰጠ ምላሽ ነው ብለዋል።
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አሜሪካ በመረጠችው መንገድ ኃላፊነት የሚወስዱትን በሙሉ ተጠያቂ ታደርጋለች ሲሉ ተናግረዋል።.
የፔንታገን ቃል አቀባይዋ ሳቢራ ሲንግ በኢራኑ እስላማዊ አብየት ዘብ በሚደገፈው ሂዘቦላ ጥቃቱ እንደተፈጸም ገልጸዋል።
ከየመን የሚተኮሱ ሚሳዔሎች የእስራኤል-ጋዛ ጦርነትን እንዴት ሊያባብሱት ይችላሉ?8 ታህሳስ 2023
ሆኖም የኢራቁ እስላማዊ ኃይል ‘ጥቃቱን የፈጸምኩት እኔ ነኝ’ ብሏል።
ይህ ቡድን ባለፈው ዓመት ብቅ ያለ ሲሆን በኢራቅ ውስጥ በኢራን ከሚደገፉ ታጣቂ ኃይሎች መካከል አንዱ ነው። ከጥቂት ሳምንታት በፊት በአሜሪካ ጦር ላይ ለተፈጸመው ጥቃት ኃላፊነት እወስዳለሁ ብሎ ነበር።
ቡድኑ ባወጣው መግለጫ ሻዳዲ፣ ተናፍ እና ሩክባ ሲል የሰየማቸውን ሶስት የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ኢላማ አድሮጎ እንደነር ጠቅሷል።
ይህ ታጣቂ ቡደን፣ በሜድትራኒያን የሚገኘው ንብረትነቱ የእስራኤል የሆነ ከነዳጅ ምርት ጋር ግንኙት ያለው ስፍራ ኢላማ ማደረጉንም ገልጿል።
በቅርቡ ከተቀሰቀሰው የእስራኤል እና ሀማስ ግጭት በኋላ የአሜሪካ ወታደር በመካከለኛው ምስራቅ ሲገደል ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
የአሜሪካ መከለከያ እንደገለጸው ከሆነ በሌላ ስፍራ የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ ጥቃት ቢሰነዘርም የተገደለ ሰው አልነበረም።
ከአራት ወራት በፊት ከተነሳው የሃማስ እና እሰራኤል ግጭት በኋላ በኢራቅ እና ሶሪያ የሚገኝ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች165 ጊዜ ጥቃት ተፈጽሟል።
ባለፈው ወር ሶስት የአሜሪካ ጦር ሰፈር ሰራተኞች በተፈጸመ ጥቃት ከተጎዱ በኋላ አሜሪካ ከኢራን ጋር ግንኙነት ያላቸውን ታጣቂ ቡድኖች ኢላማ ያደረገ የአየር ደብደባ አካሄዳለች።
ከጥቂት ሰምንታት በፊት አሜሪካ በባንግላዲሽ በፈጸመችው ጥቃት ከጥቃቱ ጀርባ ነበር የተባለ የታጣቂ ቡደን መሪ ተገድሏል።