
ከ 7 ሰአት በፊት
የአፍሪካ ዋንጫ 2023 አዘጋጅ አይቮሪ ኮስት ያለፈው ዋንጫ ባለቤት ሴኔጋልን በመርታት ወደ ሩብ ፍፃሜው ተሸጋገረች።
የ90 ዲቂቃው ጨዋታ 1 አቻ ከተጠናቀቀ በኋላ 30 ደቂቃ ቢጨመርም ሁለቱ ቡድኖች ጎል ማስቆጠር አልቻሉም።
በስተመጨረሻ በፍፁም ቅጣት ምት የተለያዩ ሲሆን አይቮሪ ኮስት በያሞሱክሮ የተደረገውን ጨዋታ በድል ተወጥታለች።
አይቮሪ ኮስት በምድብ ጨዋታ ሁለት ጊዜ ተሸንፋ ምርጥ ሶስተኛ ተብላ ነው ወደ ጥሎ ማለፍ የተሸጋገረችው።
የ90 ደቂቃው ጨዋታው ሊጠናቀቅ አራት ደቂቃዎች ሲቀረው በፍፁም ቅጣት ምት ሀገሩነ4እ አቻ ያደረገው ፍራንክ ኬሲዬ የመጨረሻውን ኳስ ወደ ጎል በመቀየር የስታደየሙን ተመልካች አስፈንድቋል።
ሃቢብ ዲያሎ ከሳዲዮ ማኔ የተሻገረለትን ኳስ በአራተኛው ደቂቃ በማስቆጠር ሴኔጋል ገና በጅምሩ እንድትመራ ማድረግ ችሎ ነበር።
- የ2023 የአፍሪካ ዋንጫ የጨዋታ ፕሮግራም እና ውጤቶች15 ጥር 2024
- የአፍሪካ ዋንጫ፡ የራስዎን ምርጥ 11 ይምረጡ27 ጥር 2024
- የስፖርት እና የታሪክ ማጣቀሻው ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ23 ጥር 2024
ምንም እንኳ አይቮሪ ኮስት ጨዋታውን ቀዝቀዝ ብላ ብትጀምርም የኋላ ኋላ ሴኔጋልን መፈታተን ይዛለች።
ለሳዑዲ አራቢያው አል ሸባብ የሚጫወተው ዲያሎ ከሳዲዮ ማኔ ያገኛትን ኳስ በደረቱ ካቀዘቀዘ በኋላ ነው ግሩም ጎል ማስቆጠር የቻለው።
ማኔ የኖቲንግሀም ፎረስቱ አማካይ ኢብራሂም ሳንጋሬ ላይ የፈፀመው ቅጣት ከሜዳ ሊያስወጣው የሚችል እንደነበር ተንታኞች ይናገራሉ።
ሴኔጋል ሁለተኛውን አጋማሽ ልክ እንደመጀመሪያው ጀምራ ሁለተኛ ጎል ለማስቆጠር ያደረገችው ጥረት አልተሳካም።
የክንፍ መስመር ተጫዋቹ ኢስማይላ ሳር ፍፁም ቅጣት ምት ይገባኛል ብሎ ለቪኤአር ጥያቄ ቢያቀርብም ምላሽ አላገኘም።
የአይቮሪ ኮስት ጊዜያዊ አሠልጣኝ የሆኑት ኤሜርሴ ፋየ በሁለተኛው አጋማሽ ሴባስቲያን አለር እና ፍራንክ ኬሲየን ቀይረው አስገብተዋል።
ከቆይታ በኋለ ተቀይሮ የገባው የቀድሞው የአርሰናሉ ተጫዋች ኒኮላ ፔፔ የሞከራቸው ሁለት ኳሶች የሴኔጋሉ በረኛ ሜንዲ ሲሳይ ሆነዋል።
ጨዋታውን የቀየረው ክስተት የሆነው ፔፔ በሴኔጋል ፍፁም ቅጣት ምት ዞን ውስጥ በሜንዲ የተሠራበት ጥፋት ነው።
የመሀል ዳኛው መጀመሪያ ፍፁም ቅጣት ምት አይደለም ብለው የሰረዙት ቢሆንም የቪኤአር ሰዎች በሰጧቸው ምክር መሠረት ለአይቮሪ ኮስት ሰጥተዋል።
ፍራንክ ኬሲየ ያገኛትን ፍፁም ቅጣት ምት ወደ ጎል በመቀየር የስታደየሙን ተመልካች አስፈንድቋል።
90 ደቂቃው ተጠናቁ ተጨማሪ 30 ደቂቃዎችም ያለጎል በመጠናቀቃቸው ሁለት ቡድኖች ወደ ፍፁም ቅጣት ምት ሊሄዱ ግድ ሆኗል።
የሰኔጋሉ ሙሳ ኒያካቴ ሲቀር ያገኘውን የፍፁም ቅጣት ምት ዕድል አለማስቆጠሩ ሀገሩን ዋጋ አስከፍሏታል።
ዝሆኖቹ በሚቀጥለው ቅዳሜ በሩብ ፍፃሜው ከማሊ አሊያም ከቡርኪና ፋሶ የሚገጥሙ ይሆናል።
ማሊ ከቡርኪና ፋሶ ማክሰኞ ምሽት 2፡00 ይፋለማሉ።
ምሽት 2፡00 በተደረገ ጨዋታ ኬፕ ቨርድ፤ ሞሪታኒያን 1-0 በመርታት ወደ ሩብ ፍቫሜው መሸጋገሯን አረጋግጣለች።