January 30, 2024 – Konjit Sitotaw 

በርካታ የኦሕዴድ አባላት የሆኑ ሰራተኞች ፈተናውን አልተፈተኑም።

በቅርቡ የአብይ አሕመድ አገዛዝ በአማራ ተወላጆች ላይ በከፈተው ዘመቻ መሰረት ከአዲስ አበባ መስተዳደር በምዘና ፈተና ስም የአማራ ተወላጆችን ለማባረር በያዘው እቅድ መሰረት በርካቶች እንደሚባረሩ ተሰምቷል። አዲስ አበባ ውስጥ ዲሞግራፊን ለመቀየር በሚል ስር እየተከናወኑ ከሚገኙት ተግባራት አንዱ የአማራ ተወላጆችን ከመንግስት መስሪያ ቤቶች ማፅዳት ነው። መረጃ ኮም ከመስተዳደሩ በሰበሰበው መረጃ መሰረት በቅርቡ በተሰጠው የምዘና ፈተና ላይ የኦሕዴድ ካድሬዎች ያልተፈተኑ ሲሆን አልፈዋል ተብሎ ስማቸው በዝርዝር ውስጥ መካተቱ ታውቋል።

ባለፈው ሳምንት የኦሕዴድ ካድሬዎች  ያልተፈተኑበት ከአዲስ አበባ መሬት ይዞታ፣ ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ ቢሮ፣ መሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ እና ከንቲባ ፅሕፈት ቤት የቴክኒክ እና የባህርይ ብቃት ፈተናውን ከወሰዱ አመራር እና ሰራተኞች ውስጥ 55 ነጥብ 61 በመቶ የሚሆኑት ምዘናውን አለማለፋቸው ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ትናንት ማምሻውን ይፋ ያደረገውን እና አዲስ ማለዳ የተመለከተችው ውጤት፤ ፈተናውን ከወሰዱ 3 ሺህ 861 ሰራተኞች ውስጥ 1 ሺህ 680 ወይንም 44 ነጥብ 39 በመቶ ብቻ የሚሆኑት ማለፋቸው ተጠቁሟል።

በፈተናውም ተገቢውን እውቀት፣ ክህሎትና ስነ ምግባር አሟልተው የተገኙ ሰራተኞች በተወዳደሩበት ቦታ የመመደብ ተግባር እንደሚከናወን የገለፀው ቢሮው በውድድሩ ከ30 አስከ 35 በመቶ ከመመዘኛ ፈተና እንደሚያዝ እና ቀሪው በመቶ ደግሞ የስራ አፈጻጸም፤ የስራ ልምድ፤ ስነ ምግባር እና መሰል ነጥቦችን ታሳቢ ያደረገ ስለመሆኑ አስገንዝቧል።

ከዚህ ቀደም በነበረው ምዘና 10 ሺሕ 257 ሰራተኞች በፈተናው መሳተፋቸውንና ከዚህም ውስጥ 5 ሺሕ 95 ማለፍ መቻላቸውን አዲስ ማለዳ መዘገቧ ይታወሳል።

እንዲሁም ከ4 ሺህ 213 ተፈታኝ አመራሮች ውስጥ 1 ሺህ 422 ብቻ ማለፋቸው ይታወቃል።