January 30, 2024 

በአማራ እና ትግራይ ድርቅ ባስከተለው ረሃብ የሰዎች ህይወት መጥፋቱን እንዳረጋገጠ የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ዛሬ ባወጣው ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

ምን ያህል ሰዎች ድርቅ ባስተከተለው ረሃብ ሞቱ ?

በትግራይ ክልል ፤ በማዕከላዊ ዞን 334 ሰው ከድርቁ ጋር በተያያዘ የሞተ ሲሆን ከዚህ ዞን ውስጥ የተቋሙ ቁጥጥር ቡድን ካየው የአበርገሌ ወረዳ 91 ሰው መሞቱን እና ከደቡብ ምስራቅ ደግሞ የኢስራ ወአዲ ወጅራት ወረዳ 17 ሰው መሞቱን ለማወቅ እንደተቻለ ገልጿል።

በአጠቃላይ 351 ሰዎች መሞታቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል ብሏል።

ከዚህ በተጨማሪ ፦
 በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀላቸው፣
 በርካታ እንስሳት መሞታቸው፣
 በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ትምህርት ቤት አለመመዝገባቸው፣
 በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ትምህርት ማቋረጣቸው በሪፖርቱ ተገልጿል።

በአማራ ክልል ደግሞ የክልሉ አደጋ መከላክልና ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባበሪያ ኮሚሽን በኩል በድርቅ ምክንያት የሞተ ሰዉ እንደሌለ ቢገለፅም በስልክ መረጃ ከተወሰደባቸው ፦
* በሰሜን ጎንደር ዞን በበየዳ ወረዳ 17 ሰዎች፣
* በዋግኸምራ ዞን በዝቋላ ወረዳ 2 ሰዎች
* በበየዳ ወረዳ 2 ህፃናት በድምሩ 21 ሰዎች ድርቁ ባስከተለው #ረሃብ መሞታቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል።

በአልሚ ምግብ እጥረት ምክንያት በበየዳ ወረዳ 23 ህፃናት ተገቢዉን ዕድገት ባለማግኘታቸዉ ሞተው መወለዳቸውም ተረጋግጧል፡፡

በአማራ ክልል አደጋ መከላክልና ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባበሪያ ኮሚሽን በኩል በድርቅ የተፈናቀለ እና በመጠለያ ካምፕ የሚገኝ ዜጋ የለም በሚል ቢገለጽም ናሙና ተወስዶ በስልክ መረጃ ከተወሰደባቸው ዞኖች እና ወረዳዎች በኩል በተገኘዉ መረጃ በድርቁ ምክንያት ፦
° የመኖሪያ ቀያቸውን የለቀቁ፣
° ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቅለዉ የሚገኙ
° በቆርቆሮ እና ኬንዳ መጠለያ የሚገኙ የተፈናቀሉ ዜጎች መኖራቸው ተረጋግጣል።

ለአብነት በዋግኸምራ ዞን በአበርገሌ ወረዳ 12270 ሰዎች፣ በሰሜን ጎንደር ዞን 9100 በላይ ሰዎች አሉ።

NB. የፌዴራል መንግሥትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በረሃብ ምክንያት የሰው ህይወት ጠፋ የሚባለው ውሸት መሆኑን እና የድርቅ አደጋ ወደ ረሃብ ተቀይሮ የሰውን ህይወት የሚያጠፋበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ የሀገሪቱ መዋቅራዊ አደረጃጀት የሚፈቅድ እንዳልሆነ መግለፃቸው አይዘነጋም።