January 30, 2024 – Konjit Sitotaw 

የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት ትናንት ምሽት በኢትዮጵያና ሱማሊያ ውዝግብ ላይ መክሯል።

ከምክር ቤቱ ስብሰባ ቀደም ብሎ የምክር ቤቱ የወቅቱ ሊቀመንበር ፈረንሳይ፣ አፍሪካዊያኑን የምክር ቤቱ ተለዋጭ አባላት አልጀሪያን፣ ሞዛምቢክንና ሴራሊዮንን እንዲኹም ጉያናን በጉዳዩ ዙሪያ በዝርዝር ያማከረች ሲኾን፣ አራቱ አገራትም ኢትዮጵያንና ሱማሊያን ማነጋገራቸው ተገልጧል።

ዓረብ ሊግና የእስልምና አገራት ካውንስል፣ የሱማሊያ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት እንዲከበር ለጸጥታው ምክር ቤት ቀደም ሲል ደብዳቤ አስገብተው ነበር።

ከዓረብ አገራት መካከል፣ የጸጥታው ምክር ቤት አባል የኾነችው አልጀሪያ ብቻ ናት።

https://theafricanstime.com