January 30, 2024 – Konjit Sitotaw 

በወለጋ ዩኒቨርሲቲ ነቀምት ካምፓስ ከትላንት ጀምሮ ይህ ዜና እየተጠናቀረ እስካላበት ዛሬ እኩለ ቀን ድረስ የመማር ማስተማር ሂደት ሙሉ ለሙሉ መቋረጡን ዋዜማ ከምንጮቿ ባሰባሰበችው መረጃ አረጋግጣለች።

ዩኒቨርሲቲው ሦስት ካምፓሶች ያሉት ሲኾን፣ ከዋናው ግቢ ነቀምት ካምፓስ በስተቀር በሻምቡና ጊምቢ ካምፓሶች መደበኛው የመማር ማስተማር ሂደት እየተካሄደ እንደኾነ ምንጮች ለዋዜማ ገልጸዋል።

በነቀምት ካምፓስ የመማር ማስተማር ሂደቱ የተቋረጠው፣ ሰሞኑን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በመላው ኦሮሚያ ጠርቶታል የተባለውን የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ የማስቆም አድማን ተከትሎ ተማሪዎች አንማርም ብለው በማመጻቸው እንደኾነ ዋዜማ ተረድታለች።