January 31, 2024 – Konjit Sitotaw 

ባለፈው አንድ ዓመት በኢትዮጵያ ሙስና መባባሱን ዓለም አቀፍ ሪፖርት አመለከተ

በተጠናቀቀው የፈረንጆች 2023 ዓመት በኢትዮጵያ የሙስና ወንጀሎች መጨመራቸውን ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል አስታውቋል።

የ180 አገራት የሙስና ነክ ወንጀሎችን በየዓመቱ የሚመዝነው ተቋም ይፋ ባደረገው የ2023 ሙሉ ዓመት ሪፖርት ኢትዮጵያ በመመዘኛዎቹ 37 ከ100 ነጥብ በማግኘት 98ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን ከትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ድረ ገጽ ተመልክተናል።

አገሪቱ በ2022 ዓመት በሙስና ነክ ወንጀሎች መንሰራፋት ልኬት 38 ነጥብ ከ100 ተሰጥቷት ከዓለም 94ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣ ነበር።

በተቋሙ መለከኢያዎችን በ180 አገራት ውጤት መሰረት ዓለም አቀፍ አማካኝ የሙስና ውጤት 43 ነጥብ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ከአማካኝ በታች በስድስት ነጥብ ዝቅ ብላ ትገኛለች።

በትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ነጥብ አሰጣጥ መሰረት 100 ማለት ከሙስና ነጻ ማለት ሲሆን ወደ ዜሮ እየቀነሰ ሲሄድ የሙስና ወንጀሎች መጨመራቸውን አመላካች ነው።

https://platform.twitter.com/embed/Tweet.html?dnt=true&embedId=twitter-widget-0&features=eyJ0ZndfdGltZWxpbmVfbGlzdCI6eyJidWNrZXQiOltdLCJ2ZXJzaW9uIjpudWxsfSwidGZ3X2ZvbGxvd2VyX2NvdW50X3N1bnNldCI6eyJidWNrZXQiOnRydWUsInZlcnNpb24iOm51bGx9LCJ0ZndfdHdlZXRfZWRpdF9iYWNrZW5kIjp7ImJ1Y2tldCI6Im9uIiwidmVyc2lvbiI6bnVsbH0sInRmd19yZWZzcmNfc2Vzc2lvbiI6eyJidWNrZXQiOiJvbiIsInZlcnNpb24iOm51bGx9LCJ0ZndfZm9zbnJfc29mdF9pbnRlcnZlbnRpb25zX2VuYWJsZWQiOnsiYnVja2V0Ijoib24iLCJ2ZXJzaW9uIjpudWxsfSwidGZ3X21peGVkX21lZGlhXzE1ODk3Ijp7ImJ1Y2tldCI6InRyZWF0bWVudCIsInZlcnNpb24iOm51bGx9LCJ0ZndfZXhwZXJpbWVudHNfY29va2llX2V4cGlyYXRpb24iOnsiYnVja2V0IjoxMjA5NjAwLCJ2ZXJzaW9uIjpudWxsfSwidGZ3X3Nob3dfYmlyZHdhdGNoX3Bpdm90c19lbmFibGVkIjp7ImJ1Y2tldCI6Im9uIiwidmVyc2lvbiI6bnVsbH0sInRmd19kdXBsaWNhdGVfc2NyaWJlc190b19zZXR0aW5ncyI6eyJidWNrZXQiOiJvbiIsInZlcnNpb24iOm51bGx9LCJ0ZndfdXNlX3Byb2ZpbGVfaW1hZ2Vfc2hhcGVfZW5hYmxlZCI6eyJidWNrZXQiOiJvbiIsInZlcnNpb24iOm51bGx9LCJ0ZndfdmlkZW9faGxzX2R5bmFtaWNfbWFuaWZlc3RzXzE1MDgyIjp7ImJ1Y2tldCI6InRydWVfYml0cmF0ZSIsInZlcnNpb24iOm51bGx9LCJ0ZndfbGVnYWN5X3RpbWVsaW5lX3N1bnNldCI6eyJidWNrZXQiOnRydWUsInZlcnNpb24iOm51bGx9LCJ0ZndfdHdlZXRfZWRpdF9mcm9udGVuZCI6eyJidWNrZXQiOiJvbiIsInZlcnNpb24iOm51bGx9fQ%3D%3D&frame=false&hideCard=false&hideThread=false&id=1752213131206533388&lang=en&origin=https%3A%2F%2Fmereja.com%2Famharic%2Fv2%2F907135&sessionId=68ba49a079f1cb8bca9b3dfebaf995c07172f371&theme=light&widgetsVersion=2615f7e52b7e0%3A1702314776716&width=550px

ተቋሙ የሚፈትሻቸው የሙስና ዓይነቶች ጉቦ፣ በጀቶችን ማዞር፣ የመንግሥት ስልጣንን ያለከልካይ ለግል ጥቅም ማዋል፣ የመንግስት አካላት በመንግስት ዘርፍ ሙስናን የመቆጣጠር ችሎታ፣ በመንግስት ተቋማት ለሙስና አጋላጭ የሆኑ አሰራሮችን፣ የመንግስት ባለስልጣናት ሃብታቸውን እና ሊፈጠሩ የሚችሉ የጥቅም ግጭቶችን ከማሳወቅ አንጻር፣ የሙስና ጉዳዮች ለሚያጋልጡ አካላት የህግ ከለላ መኖር እንዲሁም በሕዝባዊና መንግስታዊ ጉዳዮች ላይ የመረጃ ማግኘት መብትን ያካትታሉ።

የኢትዮጵያ ፌደራል ሥነ ምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ባሳለፍነው ሳምንት እንዳስታወቀው በስድስት ወራት ውስጥ 41 ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ሐብት ያስመዘገቡ ሲሆን አንዱ ብቻ ትክክለኛ ሆኖ መገኘቱን አይዘነጋም።