February 1, 2024 – Konjit Sitotaw 

በባህር ዳር የሚገኙ ሁሉም ባንኮች በኤሌክትሮኒክስ ታክስ ክፍያ ዘዴ ብቻ መጠቀም አለባቸው ተባለ።

በባህር ዳር ከተማ የሚገኙ ሁሉም ባንኮች ከጥር 2016 ዓ.ም ጀምሮ “የኤሌክትሮኒክስ ታክስ” ክፍያ ዘዴ ብቻ መጠቀም እንዳለባቸው የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው ጉዳዩን አስመልክቶ በባህር ዳር ከተማ ለሚገኙ ሁሉም ባንኮች ደብዳቤ መፃፉን ሲገልፅ ” ባንኮች ለባህር ዳር ከተማ ገቢዎች መምሪያ የሚፈፅሟቸውን ማንኛውንም ክፍያዎች በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ብቻ” ማሳወቅ እንዳለባቸው ማሳሰቡን ገልጿል።

ቢሮው ጉዳዩን በተመለከተ ከየባንኮች ዋና መስሪያ ቤት “የኤሌክትሮኒክስ ታክስ ሪፖርት” ማድረጊያ የመጠቀምያ የይለፍ ቃል (User Account) ተቀብለው ተግባራዊ እንዲያደጉ እና “በዲስትሪክቱ” ስር የሚገኙ ሁሉም ቅርንጫፎች “በኤሌክትሮኒክስ የታክስ” ስርዓት ብቻ ክፍያ እንዲያስከፍሉ ሲል አሳስቧል።

የባህር ዳር ከተማ ገቢዎች መምሪያ ከጥር /2016 ዓ.ም ጀምሮ ማንኛውንም የታክስ ማስታወቂያና የታክስ ክፍያ ቀደም ሲል በነበረው አሰራር ዘዴ ወይም “በማንዋል” እንደማያስተናግድ ሲገልፅ በመሆኑም ይህንን ባለመፈፀም ለሚመጣ ማንኛውም ቅጣትና ወለድ የባንኮች ኃለፊነት እንደሚሆን ተጠቁሟል።