February 2, 2024 – Konjit Sitotaw 

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እና መንግስት በተራዘመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ህጋዊነት እና ተመጣጣኝነት ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባቸው የመብቶች ኮሚሽኑ ኮሚሽነር አሳሰቡ።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ በይፋዊ የ’ኤክስ’ ገጻቸው ባሰፈሩት አጭር ጽሁፍ ኢሰመኮ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መራዘም “እጅግ አሳስቦታል” ማለታቸውን ተመልክተናል።

ዛሬ ረፋድ ልዩ ስብሰባ ያደረገው የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአማራ ክልል የተከሰተውን በጦር መሳሪያ የታገዘ ትግል ተከትሎ ከነሐሴ 2015 ጀምሮ የተጣለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማራዘሙ ይታወቃል።

Post

Daniel Bekele

@DanielBekele

.@EthioHRC gravely concerned about extension of emergency powers &

implications on human rights incl. the conflict casualties, humanitarian

crisis & prolonged pre-trial detentions. HPR & Gov. should duly consider

necessity, legality & proportionality of #SoE. Dialogue is the key!

·20K Views

146 Reposts 26 Quotes 263 Likes 7 Bookmarks

“የአስቸኳይ ጊዜ አዋጆች መራዘም በሰብዓዊ መብቶች ላይ ስለሚኖረው ተጽእኖ ኢሰመኮ በጣም ያሳስበዋል” ያሉት ኮሚሽነሩ የግጭቱ ሰለባዎች፣ ሰብዓዊ ቀውሶች እና ከፍርድ ውጪ በእስራት ማቆየት ዋነኛ ተግዳሮቶች መሆናቸውን አመልክተዋል።

በመሆኑም የህዝብ ተወካዮች እና መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አስፈላጊነት፣ ህጋዊነት እና ተመጣጣኝነትን በሚገባ ማጤን አለባቸው ሲሉ ኮሚሽነሩ አሳስበዋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ክትትል ኮሚቴ ባለፉት ስድሥት ወራት ውስጥ ከሰባት ሺህ በላይ ተጠርጣሪዎች መታሰራቸውን እና አምስት ሺህ የሚሆኑት ከማጣራት እና ከተሐድሶ ስልጠና በኋላ መለቀቃቸውን ገልጿል። ላለፉት 6 ወራት በዋነኛነት በአማራ ክልል ተፈጻሚ ሲደረግ የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፤ ለተጨማሪ 4 ወራት እንዲራዘም የተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወቃል ። የአዋጁን መራዘም 2 የፓርላማ አባላት ሲቃወሙት፤ 3 አባላት ጽምጽ ከመስጠት ታቅበዋል።