February 3, 2024 – Konjit Sitotaw

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት ያገኙትን ሽልማት ለማስመለስ ያለመ የተቃውሞ ፊርማ በበይነ መረብ እየተሰበሰበ እንደሚገኝ ታወቀ። የተቃውሞ ፊርማው ‘ቼንጅ’ በተባል ድረ ገጽ ላይ ‘ዩኒቲ ፎር ኢትዮጵያ’ (Unity For Ethiopia) በተሰኘ ስብስብ አስጀማሪነርት እየተከናወነ መሆኑ ተረጋግጧል።
ሽልማቱን በመቃወም የተሰባሰቡት አካላት “ሽልማቱ መሪዎች አገራቸውን በማረጋጋት እና የዜጎችን ሕይወት ለማሻሻል ላደረጉት ጥረት ማመስገን የሚበረከት መሆኑ የሚደነቅ ቢሆንም፤ አገሪቷ ያለችበት ሁኔታ ለዚህ የሚጋብዝ” አለመሆኑን በፊርማ ማሰባሰቢያው ላይ በተያያዘው ጽሁፍ ገልጸዋል።
“የመብት እና እኩልነት አቀንቃኝ” እና መንግስታዊ ያልሆነው ‘ዩኒቲ ፎር ኢትዮጵያ’ እና የተቃውሞ ፊርማውን ያነሳሱ አካላት በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል 13 ሚልየን የሚሆኑ እንዲሁም በመላው አገሪቱ ከ20 ሚልየን በላይ ኢትዮጵያውያን የምግብ ዋስትና እጦት እንደተጋረጠባቸውም አንስተዋል።
ስብስቡ አክሎም ይህ ሽልማት የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን እንዲሁም የዓለም እርሻ ድርጅት (ፋኦ) “ዘላቂ ስምና ደረጃ የሚቀንስ” ነው ያለ ሲሆን፤ ሽልማቱ “ፖለቲካዊ አንድምታ” ያለው ነው የሚል እምነት እንዳላቸውም አስታውቀዋል።
ስለሆነም የመነግስታቱ ድርጅት የምግብና እርሻ ድርጅት ለጠቅላይ ሚንስትሩ የሰጣቸውን ሽልማት እንዲሰርዝ የጠየቀ ሲሆን፤ ፋኦ ይሄን ማድረግ ከቻለ “በአመራሩ ላይ ያለውን መተማመን ማደስ፣ ለእውነት እና ለፍትህ ያለውን ቁርጠኝነት ማሳየት ያስችለዋል” ተብሏል።
Post

Petition: Revoke PM Abiy Ahmed’s Award & Demand @FAO
Acknowledge #Ethiopia‘s Humanitarian Crisis PLEASE SIGN:
https://chng.it/vqSmm2QnG5 #JusticeforEthiopia
እንዲሁም ለአለም ዓቀፉ ማህበረሰብ የሚልየኖችን ስቃይ በዲፕሎማሲያዊ ጥረት መሸፈን እና ችላ ማለት እንደማይቻል ጠንካራ መልዕክት ማስተላለፍ ይችላል ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት በሮም ጣልያን በተሰናዳ ክብረ በዓል የፋኦ አግሪኮላ ሜዳልያ መሸለማቸው ይታወሳል።