
የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሽፈራው ተክለማርያም እና የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ የኢትዮጵያ ተወካይ ራሚዝ አላክባሮቭ በጋራ ባወጡት መግለጫ; በኢትዮጵያ በቀጣዮች ጥቂት ወራት ውስጥ አስከፊ የምግብ እጥረት የሚያጋጥማቸው ዜጎች ቁጥር እንደሚጨምር ገልጸዋል።
በተለይም ከሰኔ መጨረሽ እስከ ነሐሴ ባሉት ጊዜያት ከፍተኛ የምግብ እጥረት የሚያጋጥማቸው ዜጎች ቁጥር 10 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሊደርስ እንደሚችል ጠቁመዋል።
የኤልኒኖ የአየር ንብረት ክስተትን ተከትሎ በተለይ ለኹለት ዓመታት በተከሰተው ጦርነት የተነሳ እስከ አኹን ሙሉ ለሙሉ ማገገም ባልቻሉት እና በሰሜን ኢትዮጵያ በሚገኙት ተጋላጭ ማኅበረሰቦች ዘንድ ችግሩ እንደሚያይል ተጠቅሷል።
መግለጫው፣ ቀውሱ እንዳይባባስ ለመከላከል ያለው ዕድል ጠባብ መሆኑን በመጥቀስ፣ ለችግሩ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል አስቸኳይ እርምጃ እንዲወሰድም አሳስቧል።