February 4, 2024 – Konjit Sitotaw
የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለሥልጣን፣ አገሪቱ ለአውሮፓ ገበያ የምትሸጠው የቡና ምርት አውሮፓ ኅብረት ያወጣውን አዲስ የደን ጭፍጨፋ ደንብ ያከበረ መኾኑን ለማረጋገጥ ኮሚቴ ማቋቋሙን ሪፖርተር ዘግቧል።
ኮሚቴው፣ ከባለሥልጣኑ፣ ከቡና አምራችና ላኪ ማኅበራት፣ ከቡና አምራች ገበሬዎች፣ ከኢምባሲዎችና መንግሥታዊ ካልኾኑ ድርጅቶች የተውጣጡ አባላትን እንዳካተተ ዘገባው ጠቅሷል።
አውሮፓ ኅብረት፣ አባል አገራቱ ከውጭ የሚገዙት ቡና ደኖችን በመጨፍጨፍ የተመረተ እንዳይኾን ለማረጋገጥ ያወጣው ደንብ፣ በተያዘው የአውሮፓዊያን ዓመት ተግባራዊ መኾን ይጀምራል።
ኢትዮጵያ፣ ደንቡ በኢትዮጵያ የሚኖረው ተፈጻሚነት እንዲራዘም ጠይቃለች ተብሏል። ኢትዮጵያ ባለፈው ሩብ በጀት ዓመት 117 ሺህ ቶን ቡና ለውጭ ገበያ አቅርባ 571 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አግኝታለች።