February 4, 2024 – Konjit Sitotaw

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ፣ የብሪታኒያ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንድሪው ሚቸል ከመሩት ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ጋር ትናንት መቀሌ ውስጥ መወያየታቸውን በ”ኤክስ” (የቀድሞው ትዊተር) ገጻቸው አስታውቀዋል።

ውይይቱ፣ በፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት አተገባበር ተግዳሮቶችና የጦርነቱን ተፈናቃዮች በመመለስ ዙሪያ እንደኾነ ጌታቸው ገልጸዋል።

ሚቸል፣ የኤርትራ ጦር ከትግራይ እንዲወጣ መጠየቃቸውን የዘገበው ደሞ የክልሉ ቴሌቪዥን ነው።

ልዑካን ቡድኑ፣ የመቀሌውን አይደር ሪፈራል ሆስፒታል እንዲኹም ከመቀሌ 37 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ አጉላ ከተማ የሚገኙ ተፈናቃዮችን እንደጎበኘ ዘገባው አመልክቷል።