February 4, 2024 – Konjit Sitotaw 

የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ድንበር አካባቢ በሚገኙ ኹለት ወረዳዎች እንስሳትን እየዘረፉና አርሶ አደሮችን አፍነው እየወሰዱ ስለመኾኑ ከአንድ የተመድ የዳሰሳ ሰነድ መመልከቱን ጠቅሶ አሶሴትድ ፕሬስ ዘግቧል።

ጥር 13 ቀን፣ ስምንት የትግራይ ከብት ጠባቂዎች በኤርትራ ወታደሮች ታፍነው እንደተወሰዱ ዘገባው ጠቅሷል።

ኅዳር 26 ደሞ ስድስት ሰዎችንና በርካታ ግመሎችን ጨምሮ 56 የቤት እንስሳትን መወሰዳቸውን ሰነዱ መጥቀሱን ዘገባው አመልክቷል።

የኤርትራ መንግሥት ቃል አቀባይ የማነ ገ/መስቀል ግን፣ ውንጀላውን “ሐሰት” በማለት ትናንት ማስተባበላቸውን ዘገባው ጠቅሷል።