February 4, 2024 – Konjit Sitotaw
አፍሪካ ኅብረት በተያዘው አውሮፓዊያን ዓመት መገባደጃ ታኅሳስ ላይ በሰላም ሽግግር ተልዕኮው ሥር በሱማሊያ የተሠማሩ ወታደሮቹን ሙሉ በሙሉ እንደሚያስወጣ በድጋሚ አረጋግጧል።
የኅብረቱ የፖለቲካ፣ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ይህን ያረጋገጠው፣ ከፍተኛ ልዑካን ቡድን በአገሪቱ ተገኝቶ የጸጥታ ኹኔታውን ከገመገመ በኋላ ነው።
ልዑካን ቡድኑ፣ በጉብኝቱና ከኅብረቱ ተልዕኮ መውጣት በኋላ በሱማሊያ ሊኖር ስለሚችለው የጸጥታ ኹኔታ፣ ለኅብረቱ የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤትና ለተመድ ጸጥታው ምክር ቤት ሪፖርት ያቀርባል።
የኅብረቱ ተልዕኮ፣ በሦስተኛው ዙር እስከ ሰኔ ድረስ አራት ሺህ ወታደሮችን ለማስወጣት ካኹኑ ዝግጅቱን ጀምሯል።