February 4, 2024 – Konjit Sitotaw
አሜሪካ፣ ቶም ፓሪዮሎን ለሱዳን ልዩ መልዕክተኛ አድርጋ ልትሾም መኾኗን ሮይተርስ ዘግቧል።
ፔሪዮሎ፣ ቀደም ሲል ዲሞክራቲክ ፓርቲውን በመወከል የኮንግሬስ አባልና በታላላቅ ሐይቆች አገራት የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ የነበሩ ናቸው።
ከፔሪዮሎ በፊት፣ ባኸኑ ወቅት በሱዳን የአሜሪካ አምባሳደር የኾኑት ጆን ጎድፍሬይ እና የቀድሞዋ የአሜሪካ ዓለማቀፍ ተራድዖ ድርጅት ሃላፊ ጌይል ስሚዝ ታጭተው ነበር ተብሏል።
የአሜሪካ ኮንግሬስ አባላት፣ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለሱዳኑ ጦርነት ሰላማዊ መፍትሄ እንዲገኝ የሚያግዙ ልዩ መልዕክተኛ እንዲሾሙ ሲወተውቱ መቆየታቸው ይታወሳል።
በተያያዘ፣ አምባሳደር ጆን ጎድፍሬይ በቅርቡ ከሃላፊነት እንደሚለቁ ዘገባው ጠቅሷል።