February 4, 2024 – Konjit Sitotaw
ያለ ማቋረጥ ለሳምንታት የቀጠለው በወሎ ቤተ-አምሐራ ግንባር የምስራቅ አማራ ፋኖ ተጋድሎ እንደቀጠለ ነው።
ዛሬ ጥር 25 /2016 ከወትሮው በተለየ መልኩ ታላቅ ድል በራያ ግንባር ተሰርቷል።
የፌደራል ዋናው ጥቁር አስፓልት ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ የሚወስደዉ አዉራጎዳና (መንገድ) በምስራቅ አማራ ፋኖ እጅ ከገባ ሰነባብቷል። ይህን መንገድ ለማስከፈት ጥላት ደጋግሞ ቢሞክርም የገጠመው እጣፈንታ ሽንፈትና ውርደት ሆኗል።
ዛሬ ጥላት የመጨረሻ ሀይሉን መንገድ ለማስከፈት ብሎ በሁለት አቅጣጫ ጦርነት ቢከፍትም የምስራቅ አማራ ፋኖ ክንድ እሚቀመስ ሆኖ አላገኘውም።
ከወልድያ አቅጣጫ ኦነጉ ወታደርና ባንዳዉ አድማ ብተና በኦራልና በፓትሮል ቢመጣም ጎብየን ሳያልፍ ካላኮርማ ብርጌድ አሚድ ወንዝ ላይ ሁሉም የጥላት ሃይል ከነ መኪኖቻቸዉ ተደምሥሰዋል።
ከወደ ትግራይ አቅጣጫ የመጣዉ የመጀመሪያዉ የጥላት ሀይል መንገድ ተከፍቶለት ቆቦን አልፎ መጀሎ እዲገባ ከተደረገ በኋላ መጀሎ እንደገባ ዞብል አምባ ብርጌድ ሰተት ብሎ ከተጠመደለት ወጥመድ የገባዉን የብርሃኑ ጁላ ቅጥረኛ ወታደር አሁን በዚህ ሰአት መስቀልኛ ተኩስ ከፍተው እየመቱት ይገኛሉ።
መንጀሎ ሰተት ብሎ የገባው የጥላት ሀይል ተጨማሪ ሀይል ከአላማጣ እንዲጨመርለት ቢጠይቅም ዋጃን እንዳያልፍ በሀውጃኖ ብርዴድ፥በረኸኛው ብርጌድና #ሞላ ደስዬ ብርጌድ በቆረጣ ተይዟል።
ጥላት በአሁኑ ሰአት ወደ ሰሜንም ወደ ደቡብም ወደ ምዕራብም መውጣት ሲያቅጥተው የምስራቁን ክፍል በመጠቀም ወደ አፋር ክልል ለመውጣት እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል።
ከመርሳ፥ውጫሌ፥ወርጌሳና ጊራና ምንም አይነት የጥላት እንቅስቃሴ የለም ቆንጆዎቹ የምስራቅ አማራ ፋኖ ባለሽርጡና መብረቁ ብርጌስ እየተገማሸሩበት ነው።
ጓዶች የሞቱለትን አላማ ከግብ እናደርሳለን !!