February 5, 2024 – Konjit Sitotaw
ብሊንከን ከመስከረም ወዲህ ለአምስተኛ ጊዜ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ተጓዙ
የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አቀኑ።
የጉዞአቸው ዓላማም እሥራኤልና ሀማስ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ በሚደርሱበት መንገድ ላይ ለመነጋገር መሆኑ ተገልጿል።
የእስራኤል ሀማስ ጦርነት ከተጀመረበት ከመስከረም 26 ቀን 2016 ዓም ወዲህ ብሊንከን ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ሲጓዙ የዛሬው ለአምስተኛ ጊዜ መሆኑ ነው።
ብሊንከን በአሁኑ ጉዞአቸው ሳዑዲ አረብያን እስራኤልን ግብጽንና ኳታርን ይጎበኛሉ ተብሏል።
ከጉዞአቸው አስቀድሞ በጋዛ ለተፈጠረው ሰብዓዊ ቀውስ እርዳታ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ዩናይትድ ስቴትስ በአምስት የመን በሚገኙ ሚሳይሎች ላይ የአየር ድብደባ ማካሄዷን አስታወቀች።
ከሚሳይሎቹ አንዱ የብስ ላይ ጥቃት ለመፈጸም የተሰራ መሆኑን ሌሎቹ አራት ደግሞ ፀረ- መርከብ ክሩዝ ሚሳይሎች ነበሩ ሲል የአሜሪካን ጦር አስታውቋል።
