February 13, 2024 

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ከማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ጋር በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ሁኔታ ላይ ተወያዩ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዛሬ የካቲት 5 ቀን 2016 ዓ.ም ከማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ጋር በወቅታዊ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሁኔታና ቀጣይ የቤት ሥራዎች ላይ ተወያይተዋል።

በውይይቱ የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉኀን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ሥዩም ፣ የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ መምህር ዋሲሁን በላይን ጨምሮ የሥራ አመራር ጉባኤ አባላት ተገኝተዋል።

©ማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት