February 14, 2024 – Konjit Sitotaw 

ኢትዮጵያ አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ እንዲሆን ጥሪ አቀረበች

በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው 44ኛው የአፍሪካ ኅብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብስባ ላይ ኢትዮጵያ አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ እንዲሆን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ በኩል ጥሪ አቅርባለች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ በዚሁ ጊዜ ኢትዮጵያ ያቀረበችው ጥያቄ ከአፍሪካ የ2063 አጀንዳ ጋር የሚጣጣም መሆኑንን የገለፁ ሲሆን የአፍሪካን አገር በቀል ቋንቋዎች ለማጠናከር የተያዘውን የአፍሪካ ኅብረት ግብ ጋር አብሮ የሚሄድ መሆኑንም በማብራሪያቸው አንስተዋል።

የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ቻርተር የተፈረመው አማርኛን ጨምሮ በአራት ቋንቋዎች መሆናቸውን ያነሱት አምባሳደሩ አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ ማድረግ የአፍሪካ የቋንቋ ብዝኃነት መቀበልና የጋራ ማንነትን ማጠናከር መሆኑን ጠቁመዋል።