ንጹሀን ዜጎች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት እየሞቱ ነው- ኢዜማ፣ ነእፓ እና ባልደራስ
ረቡዕ የካቲት 6 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ቃል አቀባይ “የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ያወጣው መግለጫ የቁጥር ስህተት” እንዳለው ገልጸው ፓርቲያቸው ባደረጉት ማጣራት ከ120 በላይ ንጹሀን ሰዎች መሞታቸውን “አረጋግጠናል” ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።የነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) “የሚሞቱት የንጹሀን ዜጎች ሞት ከተፋላሚ ኃይሎች በበለጠ ከፍ ብሎ ነው የሚታየው። ለዚህም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል” ሲል ለአዲስ ማለዳ አስታውቋል።የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) የሕዝብ ግንኙነት ጽህፈት ቤት ኃላፊ እዩኤል ሰለሞን በበኩላቸው “በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የማይጣሱ ተብሎ የተደነገጉ መብቶች አሉ፤ ከእነሱም ውስጥ በህይወት የመኖር መብት አንዱ ነው። ይህ ደግሞ በግልጽ እየተጣሰ በመሆኑ ደግሞ ህግን መጣስ ነው” ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መራዘምን በተመልከተ አዲስ ማለዳ ከፖለቲካ ፓርቲ አመራሮቹ ጋር ቆይታ አድርጋ ያጠናቀረችውን ሙሉ ዘገባ https://addismaleda.com/archives/36157 ያንብቡ።