
ከ 3 ሰአት በፊት
የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከቀድሞው ፕሬዚዳንት ትራምፕ ይልቅ የባይደንን ፕሬዚዳንትነት እንደሚመርጡ ተናገሩ።
ባይደን የበለጠ ልምድ ያላቸው እና ሊገመት የሚችል ባህርይ ያላቸው ሰው ናቸው ሲሉም መናገራቸው በርካቶችን አስደንቋል።
ዶናልድ ትራምፕ ለመጀመሪያ ጊዜ ለፕሬዚዳንትነት ከመወዳደራቸው በፊት ፑቲን “ታላቅ እና ጎበዝ” ሲሉም በአውሮፓውያኑ 2016 አሞካሽተዋቸው ነበር።
ባይደን የሩሲያውን ፕሬዚዳንት ፑቲንን ለዓመታት በሰላ ሁኔታ በመተቸት የሚታወቁ ሲሆን ከዩክሬን ወረራ በፊትም በአንድ ወቅት “ነፍሰ ገዳይ” ሲሉ ወርፈዋቸው ነበር።
ፑቲን በቅርቡ ከአሜሪካዊው ጋዜጠኛ ታከር ካልርሰን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይም አስተያየት የሰጡ ሲሆን ጥያቄዎቹ የሰሉ እና የተስተካከሉ ስላልነበሩ እንዳሳዘናቸውም ተናግረዋል።
ረቡዕ ዕለት ከሩሲያ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የባይደን አመራር ለሩሲያ የተሻለ እንደሚሆን የተናገሩት ፑቲን ምክንያቱንም ሲጠቅሱ “የበለጠ ልምድ ያለው፣ ሊገመት የሚችል ባሕርይ፣ ፖለቲከኛ እና መሰረት ያለው ሰው ነው” ብለዋል።
ከባይደን ዕድሜ እና የአዕምሮ ብቃት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጥያቄዎችን ውድቅ ያደረጉት ፕሬዚዳንት ፑቲን ከሶስት ዓመታት በፊት ለመጨረሻ ጊዜ ሲገናኙም የተለየ ነገር አለማስተዋላቸውን ተናግረዋል።
“በዚያን ጊዜም [ከሦስት ዓመታት በፊት] ሰዎች አቅም እንደሚያንሰው ይናገሩ ነበር እኔ ግን እንዲህ አይነት ነገር አላየሁም” ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
- አውሮፓ ራሷን ለመከላከል የሚያስችላትን የጦር መሳሪያ ለማከማቸት 10 ዓመት ያስፈልጋታል ተባለ13 የካቲት 2024
- የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲን እያንቀጠቀጠ ያለው የዢ ጂንፒንግ የፀረ ሙስና ዘመቻከ 6 ሰአት በፊት
- በናይጄሪያ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሐሰተኛ ፊርማ 6 ሚሊዮን ዶላር እንዳጭበረበሩ የተጠረጠሩ ሰዎች እየታደኑ ነውከ 5 ሰአት በፊት
አክለውም “አዎ የያዘውን ወረቀት እየተመለከተ ነበር እኔም እውነቱን ለመናገር የያዝኩትን ወረቀት እያማተርኩ ነበር። ስለዚህ ምንም የተለየ ነገር አልነበረም” ሲሉም ነው ያስረዱት።
ፐቲን አገራቸው “የአሜሪካን ህዝብ አመኔታ ካገኘ” እና የፕሬዚዳንትነቱን ቦታ ካሸነፈ ከማንኛውም መሪ ጋር እንደምትሰራም በዚሁ ወቅት አብራርተዋል።
ባይደንን ከትራምፕ ይልቅ ቢመርጧቸውም የዩክሬንን ጦርነት ያወገዙበትን መንገድ “እጅግ ጎጂ” እና “ስህተት የተሞላው” ነው ሲሉ ፑቲን ገልጸውታል።
በአውሮፓውያኑ 2016 የአሜሪካ ምርጫ ወቅር ትራምፕ ከፑቲን ጋር “በጥሩ ሁኔታ እንደሚግባቡ ጠቁመው” ነበር።
በመጪው የአሜሪካ ምርጫ የሪፐብሊካኑ ቀዳሚ እጩ የሆኑት ዶናልድ ትራምፕ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባል አገራት የሚጠበቅባቸውን መዋጮ ባለመክፈላቸው አገራቸው ከየትኛውም ወረራ እንደማትከላከልላቸው ለአንድ መሪ መንገራቸውን አስረድተዋል።
በአወዛጋቢ ንግግሮቻቸው የሚታወቁት ትራምፕ በነዚህ አገራት ላይ ሩሲያ ጥቃት እንድትፈጽም “እንደሚያበረታቱም” አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
የኔቶ ዋና አዛዥ ጄንስ ስቶልተንበርግ በምላሹ ትራምፕ የህብረቱን የጋራ ደህንነት ዋስትና “እንዳያዳክሙ” ጠይቀዋል።