
ከ 6 ሰአት በፊት
አንድጥናት የኤችፒቪ ክትባት በማህፀን በር ጫፍ ካንሰር የመያዝ ዕድልን በ90 በመቶ እንደሚቀንስ አመልክቷል።
በመላው ዓለም በርካታ ሴቶች በብዛኛው ከሚያዙበት የካንሰር ዓይነቶች መካከል የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ክትባቱ ካንሰርን እንዴት ይከላከላል?
ይህ ክትባት የተለያዩ ዘኝ ዓይነት የኤችፒቪ በሽታዎችን ይከላከላል።
ከእነዚህ መካከል የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር፣ የመቀመጫ ካንሰር፣ የመራቢያ አካላት ካንሰር እና የአንገት እና ጭንቅላት ካንሰርን ይጨምራል።
ጥናቶች እንደሚጠቁሙት፤ ክትባቱ ያገኙ ሰዎች ቢያንስ ለ10 ዓመታት በኤችፒቪ እንዳይጣዙ ይከላከላል።
ተመራማሪዎች እንደሚሉት የኤችፒቪ ክትባት በማህፀን በር ጫፍ ካንሰር የመያዝ ዕድልን 90 በመቶ በሆነ መጠን ይቀንሳል።
ክትባቱን መውሰድ ያለበት ማነው?
ሴት እና ወንድ ታዳጊዎች ለኤችፒቪ ከመጋለጣቸው በፊት ክትባቱን ቢወስዱ ይመከራል።
ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ክትባት ኢንፌክሽንን ቀድሞ መከላከል እንጂ የሰው ልጅ ሰውነት በቫይረስ ከተያዘ በኋላ ማዳን ስለማይችል ነው።
ይህ ቫይረስ እጅግ ከመስፋፋቱ የተነሳ ፆታዊ ግንኙነት ውስጥ ያልገቡ ታዳጊዎች ላይ ትኩረት ተደርጎ ክትባቱን መስጠት የግድ ሆኗል።
የዓለም ጤና ድርጅት ክትባቱ በአንድ ወይም በሁለት ዙር ሊሰጥ ይችላል በማለት፤ የበሽታ መከላከል አቅማቸው ደካማ የሆኑ ሰዎች በሁለት ወይም በሦስት ዙር ክትባቱን መውሰድ ይኖርባቸዋል ይላል።
- በኢትዮጵያ ሴቶች ቸል ስለሚሉት የካንሰር ዓይነት ምን ያህል ያውቃሉ?20 ግንቦት 2023
- ቀድሞ ከተደረሰበት በሕክምና መፍትሄ የሚገኝለትን የጡት ካንሰርን የሚጠቁሙ 12 ምልክቶች26 ጥቅምት 2023
- የካንሰር ህዋስን የሚገድለው ቫይረስ ለካንሰር ሕሙማን ተስፋ እንደሚሰጥ ተገለጸ23 መስከረም 2022
ኤችፒቪ ምንድ ነው?
ኤችፒቪ በእንግሊዝኛው ሂዩማን ፓፒሎማቫይረስ ይባላል። ብዙዎችን ለሚያጠቃ የቫይረስ ስብስቦች የተሰጠ ስያሜ ነው።
ከ100 በላይ የኤችፒቪ ዓይነቶች አሉ። ነገር ግን አብዛኞቹ ምልክት አያሳዩም።
ቢሆንም አንዳንድ የኤችፒቪ ዓይነቶች ቁስለት ሊያስከትሉ ይችላሉ። እኚህ ቁስሉ እጅ፣ እግር፣ የመራቢያ አካላት እና አፍ ውስጥ ሊከሰቱ ይችላል።
በርካታ ሰዎች ይህ ቫይረስ እንደያዛቸው ሳይውቁት ሰውነታቸው በራሱ ጊዜ አስወግዶት ምንም አይነት ሕክምና ሳያስፈልጋቸው ሊድኑ ይችላሉ።
ነገር ግን ከፍተኛ ጉዳት ሊያመጡ የሚችሉ የኤችፒቪ ዓይነቶች ያልተለመደ የቲሹ ዕድገት በማምጣጥ ወደ ካንሰር የመቀየር ዕድል አላቸው።

ኤችፒቪ ማንን ያጠቃል? በወሲብስ ይተላለፋል?
በሽታው በቀላሉ ሊይዝ ይችላል። በጣም ተላላፊ ነው። በቆዳ ንክኪ ምክንያት ሊስፋፋ ይችላል።
25 ዓመት የሞላቸው 80 በመቶ ሰዎች ለኤችፒቪ የተጋለጡ ናቸው።
ብዙውን ጊዜ በሽታው ከ18 ወራት እስከ ሁለት ዓመት ድረስ ይቆያል።
እርግጥ ነው በሽታው በወሲብ የሚተላለፍ ነው ማለት አይቻልም። ምክንያቱም ልክ እንደ ጨብጥ ያሉ በሽታዎች በወሲብ ጊዜ በሚመነጭ ፈሳሽ አይተላለፍም።
ነገር ግን በወሲብ ግንኙነት ጊዜ በሚደረግ ንክኪ የመተላለፍ ዕድል አለው።
ክትባቱ በየትኛው አገራት ተሰራጭቷል?
የዓለም ጤና ድርጅት 90 በመቶ የሚሆኑት የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር በሽታዎች የሚታዩት ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገራት ውስጥ ነው ይላል።
በእነዚህ አገራት የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ዕድገቱን አፋጥኖ ምልክት ማሳየት እስኪጀምር ድረስ መለየት አይቻልም።
የዓለም የጤና ድርጅት በአውሮፓውያኑ 2030 የኤችፒቪ ክትባትን 90 በመቶ በማዳረስ “በሚቀጥለው ምዕተ ዓመት በሽታውን” አጠፋለሁ ብሎ ቃል ገብቷል።
እንደ ድርጅቱ ከሆነ 140 አገራት የኤችፒቪ ክትባት መስጠት ጀምረዋል።

በሴቶች ዘንድ ኤችፒቪ በከፍተኛ ሁኔታ ከተሰራጨባቸው የዓለማችን ክፍሎች መካከል ከሰሃራ በታች አፍሪካ [24 በመቶ]፣ በላቲን አሜሪካ እና ካሬቢያን [16 በመቶ]፣ ምሥራቅ አውሮፓ [14 በመቶ] እና በደቡብ ምስራቅ እስያ [14 በመቶ] ናቸው።
በሽታውን ለመከታተል የሚያስችል በቂ ፕሮግራም አለመኖሩ፤ ሕክምናው የተገደበ መሆኑ እና ክትባት ለመውሰድ ማመንታት መኖሩ ለሥርጭቱ መስፋፋት እንደ ምክንያት ይጠቀሳሉ።
ሩዋንዳ ክትባቱን የማስተዋወቅ ከፍተኛ ሥራ በመሥራት ከአፍሪካ አገራት መካከል ቀዳሚዋ ናት።
በአውሮፓውያኑ 2011 ሴቶች ገና በልጅነታቸው የኤችፒቪ ክትባት እንዲወስዱ እና የማህፀን በር ጫፍ ክትትል እንዲያደርጉ ማድረግ ጀምራለች።
በመጀመሪያው ዓመት ከ10 ታዳጊ ሴቶች ዘጠኙ ክትባት እንዲወስዱ አደረገች። ባለሙያዎች ይህ ውጤት ለሌሎች አገራት ምሳሌ ሊሆን ይገባል ይሉታል።
ምንም እንኳ ክትባቱ የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር እንዳይከሰት የማድረግ አቅም ቢኖረውም፣ ከሌሎች የኤችፒቪ ዓይነቶ አይከላከልም።
ይህ ማለት̀ 5 ዓመት የሞላቸው ሴቶች በተደጋጋሚ የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ክትትል ማድረግ አለባቸው።