Mengistu Musie

  · 

Koree Nageenya (ኮሬ ነጌኛ)

ስውር አፋኝ እና ገዳይ ቡድን ወይም

የአብይ/ሽመልስ ስውር መንግስት

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ተሟጋች የተባለ ድርጅት አሸብሻቢነት

==========================================

ርዮተ የተባለ አለማቀፍ የዜና አውታር ያጋለጠው የአብይ እና የሽመልስ አብዲሳ ሚስጥር የሚያስገርም ተውኔት ግን በእውን አለም የተሰራ እና አሁንም በመካሄድ ላይ ያለው ወንጀል ነው።

ከሚያስገርመው አብይ ስልጣን በያዘ አመት 2018 (2010) የተቋቋመ የስውር ኮሚቴ ሲሆን ስሙ በኦሮሙኛ “Koree Nageenya ትርጓሜ የደህንነት ኮሚቴ” ማለት ነው። ይህ የደህንነት ኮሚቴ ቋሚ አባላት ያሉት እና በአዲስ አበባ የብልጽግና ህንጻ ውስጥ የራሱ የሆነ ቋሚ ቢሮ እና መሰብሰቢያ አዳራሽ የተሰጠው ነው። ይህ ኮሚቴ ስራ እና ተግባሩ ከሚሰራው ህግ ውጭ በተቃራኒ ስራ ያለው እና ኮሚቴው ብቻ በወሰነባቸው የሚፈጸም የፍጅት የግድያ ተግባራትን የሚያካሂድ ነው። ኮሚቴው ሲመሰረት በአብይ አህመድ እውቅና የተመሰረተ ሲሆን አብይ ወደ ጠቅላይ ሚኒስቴርነት ሲመጣ ጀምሮ ታስቦበት የተቋቋመ እንደሆነ Rueters ይናገራል። እንደምሳሌ ሁለት የወንጀል ስራወችን ጠቅሶ የከረዩ የአገር ሽማግሌወችን ግድያ እና የታዋቂውን የአርቲስት አጫሉን ግድያ እና በሱ ግድያ ዙሪያ የተካሄዱ የአፍኖ ማሰር እና የ 200 ንጹሐንን ግድያ የ Koree Nageenya ስራ እንደነበር ያትታል።

Koree Nageenya የተባለው በአብይ ሽመልስ የተመሰረተ የወንጀል እና የገዳይ ቡድን ኮሚቴ ውሳኔው የእራሱ ይሆን እና ሌላውን የግድያ አፈና እና ዳብዛ የማጥፋቱን ተግባራት በኦሮሚያ፤ በአማራ እና በሌሎች ክልሎ ይፋዊ በሆነው የየደህነት መስሪያቤት እና በመንግስት መከላከያ ትእዛዝ በማስተላለፍ ተፈጻሚ ያደርጋል።

ይህ የወንጀል ኮሚቴ በማን እንደሚመራ ርዮተር የግለሰቦችን ስም በመዘርዘር ያጋልጣል። ከ2018 ጀምሮ አብይ አህመድን ይቃወም የነበር በኦሮሞ አካባቢ የነበረውን የተቃዋሚ ክፍል በመግደል እና አፍኖ ዳብዛ በማጥፋት እየሰራ ይኸው ኮሚቴ ለመንግስት ይፋዊ በሆነ መዋቅሩ ደግሞ “ሸኔ” ገደለ በማለት የዚህን ስውር ቡድን ተግባር ለሌላ በመስጠት በዜና አውታሮች ያስነግራል። ዛሬ ይህ ቡድን ወደ አማራ ክልል በመዞር እና በአዲስ አበባ በየቀኑ ለሚታፈኑ ዜጎች ዋናው አራጊ እና ሰሪ ለመሆኑ ሌላ ግምት ውስጥ መግባት አያስፈልግም ማለት ነው። ወደአውሽ አርባ የተወረወሩ፤ በመላ ኦሮሚያ በመነኩሳት እና በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አገልጋዮች የተካሄዱ እና እየተካሄዱ ያሉ የጅምላ እና የነጠላ ግድያወች በአብይ ሽመልስ በሚመራው የዚህ ስውር መንግስት ስራ ለመሆኑ እርዮተር መልካም ዘገባ አቅርቦልናል።

አብይ ስልጣን ከያዘበት 2010 ጀምሮ በኦሮምያ ግድያ አፈና ማፈናቀል ተካሂዷል እየተካሄደ ነው። በወለጋ አያሌ ንጹሐን ተገድለዋል፤ ተፈናቅለዋል ህጻናትን ሳይቀር አማራ ናችሁ በሚል ለሞት በቅተዋል። “ወላሂ ከአሁን በኋላ አማራ አልሆንም” ያለችውን እምቦቀቅላ ልጅ ማስትወስ በቂ ነው። ማንም ይግደል የዚህ የስውር መንግስት እጅ በአንድ ወይንም በሌላ እንዳለበት ዛሬ ርዮተር ባሳየን ዘገባ ተረድተናል።

ይህን ለማረጋገጥ 2000 አማሮች በአንድ ሳምንት በተጨፈጨፉ ጊዜ አብይ አህመድ የሐገር መሪ ሆነህ ዛፍ ትተክላለህ የሚለውን የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ አበሳጭቶት ለመለሰው “ቢያንስ ይህ ዛፍ ለሞቱት ጥላ ይሆናቸዋል” የሚል ስላቁን ተከትሎ ብዙ ተችወች አብይ አህመድ በኦሮሚያ በአማራ ተወላጆች ላይ ለሚካሄደው ግድያ እጁ እንዳለበት ባለመጠራጠር የጻፉ እና ለተናገሩት ማስረጃ መሆኑ ሊዘገብ ይገባል። ይህ

ይህን የርዮተርን ዝርዝር ዘገባ አስመልክቶ ህሊናቸውን ስተው ልሀጫቸውን ያዝረበረቡ የአብይ አህመድ ገዳይ ቡድን በውጭ እና በውስጥ ደጋፊወች ምንም ያህል ያዳፍቁ እንጅ እውነታው በተጨባጭ ተገልጧ።

ርዮተር ከመሬት ተነስቶ የፈጠረው ሳይሆን የብልጽግና ከፍተኛ አባላት ከሆኑት እና በዚህ የስውር አፋኝ መንግስት ኮሚቴ የተሳተፉትን በመጠየቅ የተገኘ ሪፖርት ለመሆኑ እና “ሚልከሳ ገመቹ” አንዱ የኮሚቴው አባል ጋር የተደረገ ቃለምልልስ አንድ ሶርስ ሲሆን። ሌላው ርዮተር ያገኘውን ይህን ኢንቨስትጌሽን በመንግስት ለሚመራው የሰበአዊ መብት ተሟጋች “ዶ/ር ዳኔል በቀለ” አቅርቦለት ዳኔል እውነት ለመሆኑ ማረጋገጡን ርዮተር ያጋልጣል። አስገራሚው ትያትር በዚህ ሪፖርት የዳኔል በቀለ ድርጅት እያወቀ በሰበአዊነት ይህን ለእውቅና እንዲቀርብ ለሕዝብ አለማጋለጡ አስተዛዛቢ ለመሆኑ ታሪክ እና ግዜ የናገሩታል።

ሊዘለል የማይገባው በመቶሽሆች ያለቁበት የትግራይ ግድያ፤ በኦሮምያ በአማራ እና ኦሮሞ ዜጎች ላይ የተካሄደው ስህ እና አስርሽሆች እልቂት እና አሁን በአማራ ክልል በሰላማዊ ዜጎች ላይ ከቤት እያወጡ የሚያደርጉት ግድያ ሁሉ ከአብይ አህመድ እና ሽመልስ አብዲሳ የስውር ኮሚቴ ውጭ ላለመሆኑ አስረግጦ ሊጣፍ ሊነገር ግድ ይላል።

ይህ የስውር አፋኝ እና ገዳይ ቡድን በአብይ ችፍ ኦፍ ስታፍ በሽመልስ፤ አብዲሳ፤ በመርዳሳ፤ ፈቃዱ ተሰማ የኦሮሞ ክልል የብልጽግና አመራ አራርሳ መርዳሳ ይህን ኮሚቴ ከላይ ሆነው ከሚመሩት እና ስራውን ከሚከታተሉት ውስጥ መሆናቸውን ርዮተር ያትታል።

ይህችን መጣጥፍ ለመዝጋት ይህ የስውር አፋኝ ገዳይ መንግስታዊ መዋቅር ህግ ያላወቀው መኖሩን ዶ/ር ዳኔል በቀለ እያወቀ በዜጎች ላይ ሚሊዮኖች ሲታፈኑ፤ ሲገደሉ ከዚህ የበለጠ ወንጀል በአለም ላይ እንደሌለም እየታወቀ ትራስን ከፍ አርጎ አፍን ዘግቶ የሰበአዊ መብት ተሟጋች ነን ማለት ያሳፍራል። ሌላው የተቃዋሚወች ስብስብ የተባለ በዶክተር መስፍን የሚመራ ቧልተኛ ድርጅትም መኖሩ ማፈሪያ ከመሆን አያመልጥም። ቀልድ እና በዜጎች ደም ፌዙን አቁሞ የአማራ ክልል ፋኖ እየወሰደ ያለውን ሕዝብን የመከላከል እርምጃ በሁሉም መልክ መደገፍ ይገባል።