
2 መጋቢት 2024
ታሪካዊው የዓድዋ ድል በዓል የአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት እና ዲፕሎማቶች በተገኙበት በቅርቡ ተጠናቆ በተመረቀው የዓድዋ ድል የመታሰቢያ ሙዚየም ውስጥ ተከበረ።
128ኛው የዓድዋ ድል በዓል ለመጀመሪያ ጊዜ መሃል ፒያሳ ከአጼ ሚኒሊክ ሐውልት ፊት ለፊት ባለው ስፍራ ላይ በተገነባው ግዙፉ ሙዚየም ውስጥ ነው የተከበረው።
በሥነ ሥርዓቱ ላይ ባለሥልጣናት፣ ዲፕሎማቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን የወታደራዊ ሰልፍ ትርኢትም ቀርቧል።
በተመሳሳይ በዓሉ በታሪካዊዋ የዓድዋ ከተማ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና የክልሉ ባለሥልጣናት በተገኙበት መከበሩ ተዘግቧል።
በአዲስ አበባ የተካሄደውን የበዓሉን ሥነ ሥርዓት የሚያሳዩ ከአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ ላይ ካገኘናቸው ፎቶግራፎች የተወሰኑትን እነሆ፦
- ጉዞ ዓድዋ – የጀግኖችን ዳና የተከተሉ ተጓዦች ታሪክ2 መጋቢት 2023
- የዓድዋ ድል በዓል የሚከበርበት ግዙፉ የዓድዋ ሙዚየም ኪነ ህንጻ በዋና አርክቴክቱ አንደበት2 መጋቢት 2024
















