March 2, 2024 

የአድዋ ድል በዓልን ለማክበር ወጥተው በፖሊስ ታግተው የዋሉት 25 ጋዜጠኞች!

ነገሩ እንዲህ ነው፣ ዛሬ “አድዋን በባዶ ዕግር” በሚል መሪ ቃል ለ5ኛ ጊዜ ተገናኝተው በባዶ እግር ትንሽ ተጉዘው፣ ፎቶ  ተነስተው ለመለያየት ከፋና፣ ከኢቢሲ፣ ከአዲስ ቲቪ፣ ከሀገሬ ቲቪ፣ ከኢዜአ እና ከመንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ የተውጣጡ 25 ጋዜጠኞች በጠዋቱ ይገናኛሉ።

ይሁንና ገና 6 ኪሎ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አጠገብ ተገናኝተው “አድዋ” የሚል ፅሁፍ ብቻ ያለበትን አረንጓዴ ቲሸርት ለብሰው ፎቶ ሲነሱ የጉለሌ ፖሊስ አባላት ከበዋቸው በመንገድ ሲጓዝ የነበረ ሚኒባስ ታክሲ አስቁመው በግድ ጫኗቸው።

ከጠዋቱ 1 ሰአት የታገቱት ጋዜጠኞቹ እስከ ምሽቱ 12 ሰአት ቆይተው ተይዘው ምንም በማያዉቁት እና ባላጠፉት ነገር በሰው ዋስ አስይዘው ወጥተዋል።

ይህ አንድ ማሳያ እንጂ እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በተለያዩ ስፍራዎች ተይዘው እንደተወሰዱ፣ ማምሻውን የተወሰኑት እንደተለቀቁ፣ ሌሎቹ ግን የት እንኳን እንደተወሰዱ ቤተሰቦቻቸው እንደማያውቁ የሚደርሱኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

እውነት ለመናገር አሁን አሁን በሀገራችን የምናያቸው ክስተቶች ጆርጅ ኦርዌል “1984” በተባለው መፅሀፉ ላይ ያሰፈረውን የ dystopia የማህበረሰብ አኗኗር ሁኔታን እየመሰለ መጥቷል።

@EliasMeseret