March 3, 2024 – Konjit Sitotaw

የሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሞሃመድ ሰሞኑን ቱርክ ባስተናገደችው የዲፕሎማሲ መድረክ ላይ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ኢትዮጵያ ውስጣዊ ችግሮቿን ውጫዊ ለማድረግ እየሞከረች ነው በማለት ከሰዋል።
ፕሬዝዳንት ሞሃመድ ከመድረኩ በተጓዳኝ ዛሬ ከቱርኩ ፕሬዝዳንት ጣይብ ኤርዶጋን ጋር ተገናኝተው በኹለትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
ሱማሊያና ቱርክ ለ10 ዓመታት ይጸናል የተባለለትን የባሕር መከላከያ ስምምነት ከተፈራረሙ ወዲህ፣ ፕሬዝዳንት ሞሃመድ ከፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ጋር ሲነጋገሩ የአኹኑ የመጀመሪያቸው ነው።
ኹለቱ አገራት የባሕር መከላከያ ስምምነቱን ዝርዝር ይዘት እስካኹን ይፋ ባያደርጉም፣ ቱርክ የሱማሊያን የባሕር ወሰን ከተለያዩ የውጭ ኃይሎች ሕገወጥ እንቅስቃሴዎች ለመከላከል መስማማቷን የአገራቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።
ሶማሊላንድ ግን፣ ስምምነቱ የባሕር ወሰኔ በምትለው የውቂያኖስ ዳርቻ ላይ ተፈጻሚ ሊኾን እንደማይችል በመግለጽ ላይ ናት።